Page 1 of 1

"አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 12:24
by Revelations
አረቄው ለጦርነት ጉዞ፣ ለዘረፋ፣ ለሴት ደፈራ አገልጋይ መሆኑ አያጠራጥርም::

Please wait, video is loading...

Re: "አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 12:41
by Revelations
የተዘረፈው ለንግድ አይቀርብም ማለት ነወይ?
በሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ሥራ የተሰማራው ገብረየሱስ የሚሸጠው ጥቂት ቢሆንም በመቐለ ከተማ የሚገኝ መደብሩን ከፍቶ ይውላል። የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ ወደ ገብረየሱስ መደብር ባለፈው ሣምንት ብቅ ሲል በመደርደሪያዎች የሚታዩት ጥቂት ሸቀጦች ብቻ ናቸው። ገብረየሱስ ባዶ መደርደሪያዎቹን እየጠቆመ "በዚህ አካባቢ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የዱቄት ሳሙና የሚበላ ፓስታ ነበር። ጭማቂም ነበረበት። አሁን ስታየው ግን ምንም የለም። ከውጪ የሚገባ ነገር ምንም የለም ማለት ይቻላል። የምንሰራው ሥራ የለም" በማለት ለዶይቼ ቬለ አስረድቷል። "በጣም እየተረበሽን ነው" የሚለው ገብረየስ "እንደግፈው የነበረው እና ከእኛ ይጠብቅ የነበረው ሰው ተጨናንቆ ነው ያለው" ሲል ጫናው እስከ ቤተሰብ እንደሚዘልቅ ጠቁሟል። መደብሩን ከፍቶ የሚውለው የመቐለ ነጋዴ "እግዚአብሔር ያውቃል" እያለ መፍትሔውን ለፈጣሪው ይተዋል።

የባንክ አገልግሎት በራቀው፣ መገበያያ ገንዘብ በቸገረው እና የነዳጅ እጥረት ባየለበት የመቐለ ገበያ የንግድ ሥራ የተስተጓጎለው ግን ለወጣቱ ገብረየሱስ ብቻ አይደለም። ባለፈው ሣምንት አስራ አምስተኛ ወሩን ያስቆጠረው እና አሁንም ኹነኛ መቋጫ ያልተበጀለት ጦርነት አቶ ክፍለዮሐንስን "በተስፋ ብቻ" እንዲኖሩ አስገድዷቸዋል።

"የሸቀጦች አቅርቦት ሥራ ነው የምሰራው። እኔ በተለይም ለምግብነት የሚያገለግሉ ነገሮች፣ የተዘጋጁ ወይም የታሸጉ ምግቦችን እና የመሳሰሉትን ነበር አስመጣ የነበረው" የሚሉት አቶ ክፍለዮሐንስ "አሁን ይኸን ካቆምን ሰባት ወር አልፎናል። ምንም ነገር የለም። በሱቃችን እንደምታየው አረቄ ብቻ ነው የቀረው። ሥራ የለም ግን ዝም ብለን ከፍተንው እንውላለን" በማለት የንግድ ሥራቸው የሚገኝበትን ሁኔታ ገልጸዋል።


ገብረየሱስ ባዶ መደርደሪያዎቹን እየጠቆመ "ከውጪ የሚገባ ነገር ምንም የለም ማለት ይቻላል። የምንሰራው ሥራ የለም" በማለት ለዶይቼ ቬለ አስረድቷል።

Re: "አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 13:00
by Revelations

Re: "አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 13:14
by Revelations

Re: "አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 13:26
by Revelations

Re: "አረቄ እየጠጣን ተስፋ እየበላን እንኖራለን"

Posted: 03 Feb 2022, 20:18
by Revelations