Page 1 of 1

"ብአዴኖች ከሆዳቸው ውጭ የፖለቲካ አላማ የሌላቸው፣ በየቀኑ በጅምላ ለሚገደለው የአማራ ሕዝባቸው የማይሆኑ ተላላኪዎች ናቸው" የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ርስቱ ይርዳው

Posted: 02 Feb 2022, 09:07
by Wedi
"ብአዴኖች ከሆዳቸው ውጭ የፖለቲካ አላማ የሌላቸው፣ በየቀኑ በጅምላ ለሚገደለው የአማራ ሕዝባቸው የማይሆኑ ተላላኪዎች ናቸው" የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ርስቱ ይርዳው


Achamyeleh Tamiru

በአማራ ላይ የተጋረጠውን የኅልውና አደጋ ለመቅረፍ እያንዳንዱ አማራ ፋኖ መሆን አለበት!

በሚስጥር ተቀድቶ ከወጣው የርስቱ ይርዳው ድምጽ ብል[ጽ]ግና በሚባለው ስብስብ ውስጥ ሳይቀር አማራና ኢትዮጵያዊው ኃይል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ ድርሻ እንዳይኖራቸው ያደረገው ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረትና የሚከተለው የጉዳይ አስፈጻሚነት ፖለቲካ መሆኑ ግንዛቤ ላይ የደረሱ ስለመኖራቸው መረዳት ይቻላል። ይህንን የተገነዘቡት እነ ርስቱ ይርዳውም “አይተነው ጊዜ ወደሚያደላው” በሚለው ፍልስፍና ተክኖ “የሴም ሕዝብ የሆነው የጉራጌ ሕዝብ” አሰላለፉን ብአዴን የሚባለው ከጅብ የማያስጥል የአሕያ ባል እወክለዋለሁ ከሚለው “የሴም ሕዝብ” ከሆነው ከአማራ ሕዝብ ይልቅ ከባለጊዜዎቹ ጋር መስሎ ማደርን መመሪያ ማድረግ እንዳለበት መክሯል።

ይህ የርስቱ ይርዳው ምክር አማራን እወክላለሁ በሚለው ብአዴን በሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ላይ እንጥፍጣፊ ተስፋ ከማጣት የተሰጠ የመጨረሻ አማራጭ [the last resort] መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የሕወሓቱ ነውረኛ ድርጅት ብአዴን ጌታ ቢቀይርም ዛሬም የሚከተለው ፖለቲካ ነባር ይዞታው የሆነው ጉዳይ አስፈጻሚነት እንጂ የፖለቲካ ፍላጎት [political ambition] የሌለው፣ ከአማራ ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና እሴት የተፋታ፣ እንጥፍጣፊ ኢትዮጵያዊነት፣ ኅሊና እና ወገናዊነት የሌለው ወያኔዎች “ገ’ለን ቀብረነዋል” ያሉት አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆን ተደርጎ የተፈጠረ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ኃይሎች በደጀን እጦት እጣ ፋንታቸው የሚበላውን አዞ እንደሚመግበው ሰውዬ ከኦሮሙማ ጋር መስሎ ማደር ቢሆን የሚደረድባቸው አያደርጋቸውም።

ብአዴን የሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት የአማራም ሆነ የኢትዮጵያ መጥፊያ ትልቅ መከራ ነው። በዚህ ሰዓት ብአዴን የሚባለውን ዘግናኝ ፍጥረት ያኽል የአማራ የኅልውና አደጋ የለም። የዘጠኝ ወር የአማራ ነፍሰ ጡርን ከእርድ፤ የሰማኒያ አምስት ዓመት የአማራ መነኩሴን ከመደፈር፣ በቅዳሴ ላይ የነበሩ የአማራ ካሕናትንና ዲያቆናትን፣ በቤተ መስጂድ ሲያገለግሉ የተገደሉትን የአማራ ደረሶች፣ ኡለሞችና መሻይኾች ከፍጅት መታደግ ያልተቻለው በብአዴን ምክንያት ነው። ብአዴን እስካለ ድረስ የዘጠኝ ወር የአማራ ነፍሰ ጡር እርድ፤ የሰማኒያ አምስት ዓመት የአማራ መነኩሴ መደፈር፣ በቅዳሴ ላይ የነበሩ የአማራ ካሕናትና ዲያቆናት፣ በቤተ መስጂድ ሲያገለግሉ የሚገደሉ የአማራ ደረሶች፣ ኡለሞችና መሻይኾች ፍጅት ይቀጥላል።

ኢትዮጵያውያን ኃይሎች በመንግሥትነት የተሰየመ ደጃን እይዳይኖራቸው ያደረገው ይህ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ብቻ ሳይሆን የሕይዎት መመሪያቸውን ጭምር በልቶ ማደርን ያደረጉ የአማራ ርግማኖችና አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ የተፈጠሩ ሆዳም አማሮች ነውረኛ ድርጅት ሳይወገድ የአማራ ሕልውናም አይረጋገጥም ኢትዮጵያም አትድርንም! በአለም ታሪክ እንዲጠፋ የጥፋት ኃይሎች ሁሉ ጦርነት የከፈቱበት ሕዝብ እንደ አማራ የለም። ይህንን ለመመከትና የአማራን ኅልውና ለማስቀጠል እያንዳንዱ አማራ ፋኖ መሆን አለበት! ጊዜው የሚጠይቀው ይህን ነው። ብአዴን የሚባለውን የአማራና የኢትዮጵያ ቀዳሚ የኅልውና አደጋ ማስወገድን ጨምሮ በአማራ ላይ የተከፈተውን ጦርነት መመከትና የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ መቅረፍ የሚቻለው ይህን ጊዜው የሚጠይቀውን በማድረግ ብቻ ነው። የአማራ የኅልውና ተጋድሎ ረጅም ጊዜ ሳይወስድ ብዙ ማገዶ ሳይጨርስ ለድል ሊበቃ የሚችለው ተጋድሎው ብአዴን የሚባለውን ዘግናኝ ፍጥረት ለማስወገድ ተብሎ ከተጀመረ ብቻ ነው።

Please wait, video is loading...