የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የማስታወሻ ሐውልት ተመረቀ (ፋና ) | ከሻዕቢያ ጋር ቅራኔ ውስጥ እየተገባ ነው?
Posted: 30 Jan 2022, 10:18
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የኢፌዲሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በሆሳዕና ከተማ የተገነባውን የጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን የማስታወሻ ሐውልት መርቀው ከፈቱ፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ቤተሰቦች፣ የቀድሞ የአየር ኃይል ባልደረቦችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ለኢትዮጵያ ነጻነት ታላቅ ተጋድሎ ያደረገ ጀግና መሆኑ እየተወሳ ቆይቷል።
በተለይ እርሱ በተመደበበት የአየር ሀይል ጠላትን ድል በማድረግ ታላቅ ጀብዱ የፈጸመ ቆራጥ ታጋይ እንደነበር የቀድሞ ባልደረቦቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በሆሳዕና ከተማ የተገነባው የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሀውልትም ለእርሱ ክብር የቆመ መሆኑን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡