የተከበርክ ወንድሜ የቤተ-ክርስትያን ምሁርና የኣበሻ ልጅ ኣቶ ሃብታሙ ኣያሌው፡ የኣሜሪካ ነጮች ንግግርህን ሰምተው በ30 ደቂቃ ስነ-ልቦናህን ያውቃሉ ብለህ እባክህ ከመጠን በላይ ኣታደንቃቸው
Posted: 27 Jan 2022, 15:27
- የተከበርክ ወንድሜ የቤተ-ክርስትያን ምሁርና የኣበሻ ልጅ ኣቶ ሃብታሙ ኣያሌው፡ የኣሜሪካ ነጮች ንግግርህን ሰምተው በ30 ደቂቃ ስነ-ልቦናህን ያውቃሉ ብለህ እባክህ ከመጠን በላይ ኣታደንቃቸው ::
ተምረዋል የሚባሉ የኣሜሪካ ነጮች ከጥንት ጀምረው በኣለም በየቦታው እየሄዱ ኣህያም የማያደርገው ስህተትና ኣራዊት የማያደርገው ግፍ ያደረጉ ናቸው ። የኣሜሪካ ነጭ መሪዎች የመምዘን ችሎታ የላቸውም ። ወያኔ የኢትዮጵያ መንግስት ኣውድቆ ኣዲስ ኣበባና ኢትዮጵያ ይቆጣጠራል ብሎ እንደ ጦጣ ከዛፍ ወደ ዛፍ እየዘለለ ኣሜሪካውያኖችና ሌሎች ነጮችን ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ይገፋፋ የነበረው ማን ነው ? በሰላሳ ደቂቃ የሰውን ስነ-ልቦና ኣዋቂው ኣሜሪካዊው ነጭ ወይስ ጦጣና የጦጣ ልጅ ?
ኣሜሪካውያን የጻፉትን የሒሳብና ሌሎች መጻህፍቶች በመላ ኣለም ተማሪዎች እንደሚማሩበት የታወቀ ነው ። ኣሜሪካ የእውቀት ኣገር መሆኑም የሚክድ ሰው የለም ሆኖ ግን የኣሜሪካ ነጭ መሪዎች ልዩ የመምዘን ችሎታ ኣላቸው ኣይባልም ። ኣንተ በገዛራስህ ከነ ድክመትህና ጥንካሬህ በጭንቅላትህ ከየዋይት ሃውስ ኣማካሪዎች እንደምትበልጥ ምንም ጥርጣሬ የለኝም።