ዬምር ዬምር! የብርሃን ግነት! የፀሃይ ንጋት! የብርሃን ልደት! የልጃገርዶች ፌስቲቫል !!!
Posted: 19 Jan 2022, 01:16
የወንድ ልጆች የገና ጨዋታ አንቃት ይባላል ። አንቃት (አንጋት ገና፣ ንጋት፣ ልደት ማለት ነው ። ወንዶቹ የገና ዱላ ይዘው ሆያ ሆዬ ከቤት ቤት የሚዞሩት እንዞሪቴ ይባላል ። በሌጣ ትርጉሙ እንዞሪቴ ከቤት ቤት መዞር ማለት ሲሆን ልጆች በየቤቱ እየዞሩ የብርሃን መወለድን የምስራች የሚያበስሩበት ባህል ነው ። ነገር ግን ኢዮ እንዞሪቴ ገና ነበቦ ማለት ሌላ ትርጉሙ እነሆ እንደ ኦሪት ገና አበበ፣ ፍጥረት ደራ፣ በራ ማለት ነው ! ቦ በራ! ሆነ ተከሰተ! ቦ ዬቦ ሆነ ማለት ነው!! ግዕዝ ነው !!