Page 1 of 1

ስንት ማፈሪያ አለ? ኢትዮጵያ ከአጎዋ በመሰረዝዋ ወደ 78% የሚሆን የቆዳ ውጤት ወደ ውጭ መላክ አልቻለችም

Posted: 16 Jan 2022, 13:42
by Abaymado

እነዚህ ሰዎች የሚያስብ ጭንቅላት አላቸው ወይ? ሁለመናቸው ከ ሀ እስከ ፐ የተሰራው በእርዳታ ነው:: በሰው ትከሻ ካልኖሩ ያማቸዋል::

78% የቆዳ ምርት የተባለው ጫማ እና ሌሎች የቆዳ ውጤቶች ናቸው :: ይህን እኮ አገር ውስጥ ገበያውን እንዲቆጣጠር ማረግ ይቻላል:: በተለይ 100 ሚልዮን ሕዝብ የአገሪቱን ጫማ እንዲገዛ ማስገደድ ነው :: ሌላ ምን ይፈልጋሉ? የውጭውን ገበያ ማስወጣት ነው:: ደሞም እኔ እስካሁን የምገዛው የአገር ምርት ነው: ጥራትም አለው::

ከአጎዋ የቀረባቸው 200 ሚልዮን ዶላር አይደል? ይህ በሌላ መንገድ መተካት አይቻልም?

ለዚህ ነው ተዋርደው የሚያዋርዱን?
አያቶቻችን እንዲህ የተዋረዱ እና እኛን የሚያዋርዱ አልነበሩም ::