ጀግናዋ ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አንጸባራቂ ኮኮብ
Posted: 12 Jan 2022, 22:31
አትሌት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈች
–
ጀግናዋ አትሌት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ለተፈቱት እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ቀለብ ስዮም እና አስካለ ደምሌ” እንኳን ደስ ያላችሁ፤እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ” በማለት መልካም ምኞቷን ገልፃለች።
–
አትሌቷ ከእስር ለተፈቱት አመራሮች መጭው ጊዜአቸው የተቃና እንዲሆን እና ኢትዮጵያም ሰላሟ፣አንድነቷ እና ክብሯ እንዲመለስ ያላትን ምኞት ገልፃለች።
የባልደራስ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በበኩሉ አትሌት ሽህ አለቃ ደራርቱ የፓርቲው ፅ/ቤት ድረስ ቃሏን አክብራ በመልካም መንፈስ በመገኘት ይህንን እውቅና በመስጠቷ ከልብ አመስግኗል።
–
በተጨማሪም “በቀጣይ በኢትዮጰያ ሰላምና ልማት ይሁን። ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል።
ሌሎች ከእስር የተፈቱ የፓርቲው አመራሮች አትሌቷ ቃሏን አክብራ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት “የእንኳን ደስ ያላችሁ”መልዕክት በማስተላለፏ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።