የጉልበቱን መንገድ እድሜ ከስግብግብነት ውጭ የተለየ ዓላማ ለሌለው ጀንፈል አበላሽተውታል።
የራያ አካባቢወችም ወሎየነታቸውን አክብረው ወሎ ራሱን ችሎ በሚፈጥረው አስተዳደር ማዕቀፍ ብቻ ይመለሳሉ።
ከሁሉም በላይ እንደ አገርም ትልቅ አስተዋጽኦና ዋጋ ያለው የወልቃይት ሁመራ፣ ጠገዴና ጠለምት አካባቢወች በበጌምድር/ጎንደር እቅፍ ስር መሆናቸው ነው። በዚህ ምክንያት የአማራ አንድነት ይሸረሸራል የሚለው የፖለቲካ ደንቆሮ ብቻ ነው። አማራነት በፖለቲካ አስተዳደር የተፈጠረ ማንነት አይደለም። ተከፋፈለም ከተባለ የተከፋፈለው አሁን በአንድ ላይ ሆኖ ነው። በዚህ ምክንያት የሚጎዱት ኮንትሮባንዲስቶችና ኮንትሮባንዲስቶች የሚዘውሯቸው ፖለቲከኞች ነው፤ ተጠቃሚው ደግሞ ሕዝቡ ነው። ያው መሆኑ ለማይቀር ነገር መሽኮርመምና ፍርሀት ትርጉም የለውም።
Please wait, video is loading...