Page 1 of 1
ኮሎኔል አብይ አህመድ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ባሳየው ተሳትፎ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ፓርላማው እንድ ሰጠው አስገንዝበህ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ብርሃኑ ጁላ ይህን ማዕረግ ተሰጥቶታል
Posted: 08 Jan 2022, 12:14
by Abere
ሆረስ፤
ኮሎኔል አብይ አህመድ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ባሳየው ተሳትፎ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ፓርላማው እንድ ሰጠው አስገንዝበህ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ብርሃኑ ጁላ ይህን ማዕረግ ተሰጥቶታል። ብዙዎች እያፌዙበት ነው በማዕረጉ አሰጣጥ እና የሰውየው የጦር ብቃት። ምናልባት ፊልድ ማርሻል አዲሱ የወደ ፊት የሚሊቴሪ Rank ዲፕሎማ ሚል (Diploma mill/ ይሆን? በወያኔ ዘመን ዶክትሬት እና ማስትሬት የድፕሎማ ሚል ነበሩ። እነ ሳሙራ ዮኒስ እና አባዱላ ገመዳ የማስትሬት እና ዶክትሬት ድግሪ ገዝተዋል ሲባል ሰምቸ ነበር።
Re: ኮሎኔል አብይ አህመድ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ባሳየው ተሳትፎ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ፓርላማው እንድ ሰጠው አስገንዝበህ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ብርሃኑ ጁላ ይህን ማዕረግ ተሰ
Posted: 08 Jan 2022, 12:38
by Horus
Abere wrote: ↑08 Jan 2022, 12:14
ሆረስ፤
ኮሎኔል አብይ አህመድ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ ባሳየው ተሳትፎ የፊልድ ማርሻል ማዕረግ ፓርላማው እንድ ሰጠው አስገንዝበህ ነበር። ያ ሳይሆን ቀርቶ ብርሃኑ ጁላ ይህን ማዕረግ ተሰጥቶታል። ብዙዎች እያፌዙበት ነው በማዕረጉ አሰጣጥ እና የሰውየው የጦር ብቃት። ምናልባት ፊልድ ማርሻል አዲሱ የወደ ፊት የሚሊቴሪ Rank ዲፕሎማ ሚል (Diploma mill/ ይሆን? በወያኔ ዘመን ዶክትሬት እና ማስትሬት የድፕሎማ ሚል ነበሩ። እነ ሳሙራ ዮኒስ እና አባዱላ ገመዳ የማስትሬት እና ዶክትሬት ድግሪ ገዝተዋል ሲባል ሰምቸ ነበር።
ሰላም አበረ፣
እኔ በፓርላማ የቋቁሞ የመጀመሪያው ተሸላሚ ይሁን ያልኩት The Order of Lion of Africa የአፍሪካው አምበሳ ሜዳል የሚል ነው። እኔ ሚሊታሪው ውስጥ ቢሿሿሙ ግድ የለኝም፤ የራሳቸው ራንኪንግ ሲስተም ስላላቸው ማለት ነው ። ዐቢይ ብሄራዊ ሽልማት እንጂ ወታደራዊ ማ ዕረግ ሊሰጠው አይገባም! ሲቪል መሪ ነው።
ሌላው መጠንቀቅ ያለብን ዲዳክሽኒስት አለመሆን ነው ። ዛሬ ስብሃት ነጋ የሚባል መሰሪ የትግሬ ባንዳ፣ ኢትዮጵያን ለ50 አመት የወጋ ከሃዲን ስንት ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ቤትና ሚስታቸው ጥለው ሞተው ከዋሻ ያወጡትን ውንጀለኛ አጉል ሰላምና ድርድር በሚል አላዋቂ ውሳኔ አብይ ይህን መሰል ረግረግ ውስጥ መመልሱ እኔን ከማናደድ ይልቅ አሳዝኖኛል! በአሜሪካኖች ግፊት ጽናቱን ሰብረውት ሊሆን ይችላል። አንዳዴ ደሞ ከልክ በላይ ያሸናፊነት ስሜትም ወደ ግዙፍ ስህተት ይወስዳል ።
ዞሮ ዞሮ ከብሄራዊ ውይይቱ እስክንድርና ጃዋርን በፍታቱ ብልህነት ነበር ። መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ለ30 አመት የታገላቸውን እንጀለኞች ጦር እየወጉ ባሉበት ወቅት አለምንም አጥጋቢ ማብራሪያ መፍታት ይህን ሁሉ የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ትግል መስደብ አድርጌ ነው የማየው
አቢይ አህመድ በግልጽ ወጥቶ ስህተቱን አምኖ ኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለበት ብዬ አምናለሁ !