Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15482
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የዘንድሮ ገና ዘንዶ እና እርግብ እኩል ምህረት ሊያገኙ ነው። ንጉሥ ሆይ! በነካካ እጅዎ አቤቱ እነ ስብሃት ነጋን ከዘንዶዎቹ ጁሃር እና በቀለ ገርባ አትለያቸው።

Post by Abere » 07 Jan 2022, 12:08

የዘንድሮ ገና ዘንዶ እና እርግብ እኩል ምህረት ሊያገኙ ነው። ንጉሥ ሆይ! በነካካ እጅዎ አቤቱ እነ ስብሃት ነጋን ከዘንዶዎቹ ጁሃር እና በቀለ ገርባ አትለያቸው። ያች መናጢ ድሮን ትግሬ እንጅ ኦሮሞ ማየት አትችልም ሲባል ሰምቻለሁ። እርስዎስ?

Abere
Senior Member
Posts: 15482
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የዘንድሮ ገና ዘንዶ እና እርግብ እኩል ምህረት ሊያገኙ ነው። ንጉሥ ሆይ! በነካካ እጅዎ አቤቱ እነ ስብሃት ነጋን ከዘንዶዎቹ ጁሃር እና በቀለ ገርባ አትለያቸው።

Post by Abere » 07 Jan 2022, 12:24

ህግ እና ሰብዐዊ ሞራል ብቃት ባነሳቸው ሰዎች እጅ ሲወድቁ የወንበደዎች እና የቀማኞች መጠቀሚያ ይሆናሉ፤ትሁታን እና ግፉዓን ይብለጥ ይጎዳሉ። ይበልጥም ተጠቂ ይሆናሉ። በእውነት ጅሃር እና በቀለ ገሪባ ከእስራት መፍታት ማለት በእነርሱ ምክንያት ህይወታቸው የጠፋ የሻሸመኔ፥ ሀረርጌ፥ ወለጋ፥አሩሲ፥ወዘተ ኢትዮጵያዊያን እና ብዚህም የተጎዱ ቤተሰቦቻቸው ላይ መሳለቅ አይደለም ወይ? እነዚህን ወንጀለኖች መልቀቅ ከእግዚአብሄር ጋር መጣላት አይሆንም ወይ? ገና ወይም የጌታችን ብርሃነ ልደት ማለት ምህረት ነው ማለት ቢሆንም ከሳጥናኤል ጋር የሚመሳሰሉ ወንጀለኞች ይህን አጋጣሚ መጠቀም ማለት የቅዱሳኑን መስዋዕት ዓሣማ ወይም እርያ እንደ በላው ይቆጠራል። ቢዚህ አካሄድ ከሆነ ወድፊትስ ወንጀለኛን ለምን ለህግ ማቅረብ አስፈለገ? ህግ በሌለበት አገር ደግሞ መንግስት የለም ማለት ነው። የህዝብ መንግስት ሳይሆን የቡድን መንግስት ነው ያለው ማለት ያስችላል።

Post Reply