Finfinne Times
የትግራይ ሰራዊት ተቆጣጥሯቸው ከነበረው ስፍራዎች እንዲወጣ ዋነኛ ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ነው ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን በራሳችን ፍላጎት አዲስ አበባ ገብተን ስርዓቱን እና የስርዓቱ አቀንቃኞችን ማጥፋት እንችል ነበር።
ነገር ግን የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ይህን እንዲናደርግ ስላልፈለገ ነው የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ፍላጎቱን ያማከለ ውሳኔ ወስነን ወደ ትግራይ የተመለሰው ብለዋል።
ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ከአደራዳሪዎች ምን ይፈልጋሉ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ደብረፅዮን ተኩስ በይፋ እንዲቆም እና በሰው ሰራሽ ረሃብ እያለቀ ያለው ህዝባችንን የሚታደግ የሰብኣዊ እርዳታ እንዲገባ እንፈልጋለን ሲሉ ነው የገለፁት። .... ዶ/ር ደብረፅዮን ለCNN ከተናገሩት
ሳሳጥረው TDF ምዕራብ ትግራይን ብቻ ነው ከዚህ በኃላ የሚቆጣጠረው። ሌላ የጦርነት ሂደት በጭራሽ አይኖርም። ወደ ፊንፊኔ ደርሶ የተመለሰው ሰራዊት በአለምአቀፉ ማህበረሰብ አስተማማኝ የድርድር ማሰሪያ ውል ካልቀረበለት በስተቀር በፍፁም አያፈገፍግም። በፍፁም ...
ድርድሩን የምትመራው ሀገረ አሜሪካን ናት። TDF አፋርና አማራ ክልልን ከለቀቀ በኃላ በአሸናፊነት መንፈስ ገስግሶ ትግራይ ሳይገባ የቆመው የመከላከያ ሰራዊት በአሜሪካን አደራዳሪነት የተሰጠውን ውል ነው ያከበረው።
ሌሎች ነገሮችም በእርግጥ ይኖራሉ። በዋነኝነት ግን ሁለቱ ነጥቦች ወሳኝ ናቸው። አሁን ዶክተር ደብረፅዮን ባነሱት ነጥብ ጦርነቱ እንዲቆምና ተኩስ አቁም እንዲደረግና የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ጠይቀዋል።
ዛሬ የአሜሪካን የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ፌልትማን ፊንፊኔ ይገባል። Almost TDF ምዕራብ ትግራይን እየተቆጣጠረ ነው። በጣም በቅርቡ ከምዕራብ ትግራይ መያዝ በኃላ የተኩስ አቁም ይደረጋል። በእርግጠኝነት
ዶ/ር ደብረፅዮን ጦርነቱ እንዲቆም ጠይቀው .. ጠ/ሚ አብይ አህመድ ደግሞ ጦርነቱን በእርቅ እንጨርሰው ብሎ ተናግሮ ... የሚቀጥል ጦርነት በእርግጥም አይኖርም። ነገር ግን ብዙ ደጋፊዎች ጦርነቱ ቀዝቅዞ እያዩ ካልቀጠለ እያሉ ነው
ይህ የሆነበት ምክንያት በጦርነቱ በተፈጠረው የስነልቦና ጠባሳ ምክንያት ነው። ማንነትህን አጥፍቶ አንተን ሊቀብርህ የሞከረ ስርዓት ጋር የሚደረግ ንግግርና ድርድር ማንም ቢሆን የመቀበል ሞራል ሊኖረው አይችልም።
ነገር ግን ዋናው ያንተ ሞራል ሳይሆን .. ያለው ተጨባጭ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲያዊ ወታደራዊ አለምአቀፋዊ ሁኔታዎች ናቸው። ከዚህ አንፃር ጉዳዩ የሚዘጋው በጠረጴዛ ዙሪያ ነው። ድርድሩ ሊዘገይ የቻለበት ወይም በተለያዩ ሂደቶች እያለፈ የሚገኝበት ሁኔታም የህዝቡን ስሜት ለማቀዝቀዝ ስለተፈለገ ነው።
Finfinne Times
https://www.facebook.com/permalink.php? ... 1731586155