Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Agames losing their Minds! Noble Amhara in Metemma signing Peace deal with Sudan Against TPLF

Post by Noble Amhara » 05 Jan 2022, 02:12


የኢትዮ ሱዳን ግንኙነት በጠነከረ መልኩ ለማስቀጠል በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ከተማ አስተዳደር የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮች ና የሱዳን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ዉይይት ተደረገ።
የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሲሆኑ የውይይቱ መሰረታዊ የሆኑት ሀሳቦችም በእርስ በርስ ግንኙነት ዙሪያ ያሉ የግብይት እንቅስቃሴ ላይ እንደፈለጉ የሚዘጉበትና ሲፈለግ የሚከፈትበት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ብንነጋገር የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።
ከሱዳን የተገኙት ከፍተኛ አመራርም የሰጡት ምላሾች ሁለቱም ህዝቦች ከምንም በላይ የሚዋደዱና የጠበቀ ግንኙነት እንዳለ ተናግረዋል።
ከምንም በላይ ሁለቱን ሀገራት ግንኙነታቸዉን የበለጠ ሊያጠናክር የሚያስችል ውይይት ለማድረግ በመገናኘታችን በጣም ጥሩ መሆኑን አብራርተዋል።
በሱዳን ቀጠናዎች ዙሪያ የሚገኙ ጁንታዎች፣የጉምዝ፣የቅማንት ፅንፈኛና ኦነግ ሸኔ በዙሪያው እንደሚገኙና በሱዳን ዉስጥ በመመሸግና መነሻቸዉንበማድረግ በኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ለማድረስ ተደጋጋሚ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አስታዉሰዉ ገር ግን ይህን ችግር ልንፈታው የምንችለው እየተነጋገርንና የጋራ የሆነ መግባባት ሲኖር ነው።ስለዚህ ይህን በዙሪያው የሚገኙ የሁለቱም ህዝቦች የጋራ ጠላቶች በመተባበር ማስወገድ ይኖርብናል።
በአጠቃላይ ኢትዮና ሱዳን መቸም ቢሆን ለግጭት የሚዳርግ ነገር የሌለን ቢሆንም የሁለቱን ህዝቦችና መንግታት ግንኙነት ሊያሻክሩ የሚችሉ ነገርች ቢኖሩ እንኳን በመነጋገር መፍታት ይኖርብናል።
በተጨማሪም አቶ ደሳለኝ ጣሰው እንደተናገሩት የሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ምን መሆን እንዳለበት በሚለው ዙርያ የመወያያ ሀሳቦች እንዲሆን ፍላጎታቸዉ መሆኑን አስታዉቀዋል።
በሁሉም ህዝቦች ግንኙነቱን ለማድረግ ፍላጎታችን ከድንበር ከተሞች በዘለለ እስከ አዲስ አበባና ካርቱም ድረስ ለማዝለቅ ፍላጎት እንዳላቸው የሱዳኑ የጦር መሪ ብር/ጀነራል በሽር ሰኢድ ገልፀዋል።
በሁለቱም ህዝቦች መካከል ከመፋቀርና በጋራ ተባብሮ ከመኖር ዉጭ ምንም አይነት ቅራኔ እንደሌላቸው አብራርተዋል።
የንግድ መጀመሩን አይተናል ነገር ግን በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥልና ተቋርጦ የነበረዉ የሁለቱ የድንበር አካባቢ ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲቀጥል እኛም ፍቃደኛ ነን ሲሉ ሀሳባቸዉን ሰንዝረዋል።
የሱዳን ጉሙርክ ኃላፊ አህመድ ሰኢድ እንደተናገሩት ከባድ የጭነት ማጓጓዣዎች ገብተው የንግድ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን አብራርተል።
ግንኙነቱ የበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥላል ስለዚህ ያለው የሱዳንና የኢትዮጲያ መከላከያ፣ልዩ ሀይል ፣ፖሊስ ፣ሚኒሻ አካባቢያችንን በተጠናከረ መልኩ የሁለቱ ህቦችን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቸዉም በላይ የመስራት ሀላፊት አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።

መተማ ከተማ ኮሙኒኬሽን
26/04/2014ዓ.ም


Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...