የኢትዮጵያ ዝርያዎች በአገርም ሆነ አባይ ማዶ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ አንድ ገና ስም ያልተሰጠው ሶሺያል ንቅናቄ ወይም ሶሺያል አብዮት እያስነሱ ነው። የዚህ ንቅናቄ መንፈስ፣ የዚህ አብዮት ልብ ትርታ ኢትዮጵያዊነት በሚለው ጽንሰ ነገር፣ ጽንሰ ሃሳብና ፍልስፍና ላይ ያረፈ ነው።
የዚህ ታሪካዊ ክስተት እና ቀጣይ እድገቱ ምን እንደ ሆነና እንደ ሚሆን ይህ በህይወት ያለው ትውልድ ወደፊት የሚያብራራው ፣ የሚፈላሰፍበት፣ ንድፈ ሃሳብና ትግበራ የሚቃኝበት ይሆናል። ክስተቱ ግን ተከስቷል ።
በከፍተኛ ደረጃ በመንቃት ላይ ያሉት ትውልዶች ይህችን አገር አሁን ካለችበት ታሪካዊ ሁኔታና ቁመና ወደ ሌላ አይነት እውነታና ቁመናል ሊለውጧት አገራዊና ህዝባዊ ቃል ኪዳን በአንድነት እየገቡ ነው።
በእኔ እምነት ይህን ክስተት፣ ይህን አገር አቀፍ አለም አቀፍ መነሳትን በትክክል የሚገልጸው ቃል የኢትዮጵያ አብዮት የሚለው ነው።
የኢትዮጵያ አብዮት ማለት ምን ማለት ነው?
ከ1976 እስከ ዛሬ 2021 የኢትዮጵያ ወጣትና ሕዝብ ፍላጎት ኢትዮጵያ አሳድጎ በኢትዮጵያ መኖር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ወጥቶ መለወጥ፣ መበልጸግ ነበር ። ለድፍን 50 አመታት ይህ ወደ ወጭ የመመልከት ሳይኮሎጂ ኢትዮጵያ ሲያዳክም ለማኝ ሲያደርግ የነበረ ፓራዳይም አሁን እየፈረሰ ነው ።
ይህ ወደ ውጭ መመልከት፣ መለመን እና ራስን መክዳት ያመጡት ቅኝ ገዥ አውሮፓና አዲስ ቅኝ ገዥ አሜሪካ ናቸው ።
አሁን የተነሳው የአብዮት መሪ ፍልስፍና አንድ ኢትዮጵያዊ ያለው ምኞት ካገር ተሰዶ እንግሊዝ መሆን፣ አሜሪካዊ መሆን፣ ሱድናዊ መሆን አይደለም፤ በተቃራኔው እንግሊዝን፣ ኢትዮጵያን ፣ ስዊድንን ወደ ኢትዮያ ማምጣት ነው ። ይህ ነው የዲያስፖራ ወዳገሩ መመለስ ምስጢር።
እስከ ዛሬ ኢትዮጵያዊያን የምንታወቅበት ታሪክና ባህል ያውሮፓ ተገዥነትን መቃወም ነበር ። አሁን ያለው የኢትዮጵያ ታሪክና አላማ ራሳችንን እንዳውሮፓ ማጠንከር፣ እንዳውሮፓ ማደግ ፣ እንዳሜሪካ መሆን ነው ።
ይህ ትልቅ የሳይኮሎጂ ለውጥ ነው ። ወደ ውጭ መመልከት ቆመ፣ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወደ ወስጥ መመልከት፣ መሰብ፣ ራሱን ትልቅ ብልጽግ አገር ለማድረግ አንድ ቃል ኪዳን ላይ እየደርሰ ነው ።
በአ ሆረስ