Page 1 of 1

ኣሁን ከድሉ ጎን ለጎን ትምህርት መሰረት ያደረገ የኢትዮጵያ ዳግመ-ትንሳኤ መመስረት ኣለበት። በነጮች የምትናቀውና የምትገደለው ዘመናዊ እውቀት የራስህን ስላላደረግህ ነው።

Posted: 22 Dec 2021, 13:30
by Abe Abraham


  • ጓላ-ቀርነት የራሱ መዘዝ ይጠራል

    ኣሁን ከድሉ ጎን ለጎን ትምህርት መሰረት ያደረገ የኢትዮጵያ ዳግመ-ትንሳኤ መመስረት ኣለበት። በነጮች የምትናቀውና የምትገደለው ዘመናዊ እውቀት የራስህን ስላላደረግህ ነው። ግብጻውያን የሃይማኖት ኣባቶችና ሊሂቃን ከየፈረንሳ ዘመቻ ( ኣል-ሓምላ ኣል-ፊረንሲያ ) በጓላ ተመሳሳይ ጥያቄ ኣንስተው ነበር ምክንያቱ ጥቂት መሳርያ የያዙና በተለያየ የእውቀት መስኮች ፈሊጣዎች የሆኑ - የሃገሪቱን ታሪካዊና ተፈጥሮኣዊ ይዞታ ለመመርመር - ኣገሩን በቀላል ወረው ስለ ገቡ ።

    በየመንደሩ ስንት እንክብካቤ ያላገኘ ጭንቅላት ያለው ህጻን ይኖር ይሆናል ? በትምህርት ብቻ ሳይሆንም ለምሳሌ በእግር-ኳስም ሊሆን ይችላል ። ልዩ ችሎታ ( ታለንት ) በየክለብ ደረጃ በሚጫወቱ ንቁ ( ኣክቲቭ ) የሆኑ ሰዎቻ ብቻ ሊታጠር ኣይችልም ። በኣጭሩ ከንግዲህ በጓላ የኣስተሳሰብ መቀየር ሊያስፈልግ ነው ። ኣንዳንዶች እንግሊዘኛና ኣማርኛ የሚደባልቁ እንደ ሚሉት ፥ It is a must !!



.

Re: ኣሁን ከድሉ ጎን ለጎን ትምህርት መሰረት ያደረገ የኢትዮጵያ ዳግመ-ትንሳኤ መመስረት ኣለበት። በነጮች የምትናቀውና የምትገደለው ዘመናዊ እውቀት የራስህን ስላላደረግህ ነው።

Posted: 23 Dec 2021, 16:15
by Abe Abraham
  • ዘመናዊ እውቀት - በተለይ ማተማቲክስና ፍዚክስ - ተምረህ እውቀቱን የራስህን ማድረግ በጣም ኣስፈላጊ ነው ።

    ኣንድ ሩስያዊ የማተማቲክስ ኣስተማሪ ለብዙ ጊዜ በኣሜሪካ ዩኒቨርስቶች ካስተማረ በጓላ ስለ የማተማቲክስ ተማሪዎችና የትምህርት ዓይነቱ የማስተማር ዘዴ በንዴት ኣንድ ጽሑፍ ኣቅርቦ ነበር ። ያናደደው ነገር ይህ ነበር ፥ ብዙ ተማሪዎች ለብዙ ኣመታት ማተማቲክስ ተምረው የማተማቲካዊ ኣስተሳሰብ ግን ኣያውቁም ። :lol: :lol:

    ሄንድሪክ የተባለና እንደ የኣፓርታይድ መስራች የሚታወቀው ኣራዊት ኣንድ ጊዜ እንዲህ ኣለ ፥ ጥቁሮችን ማተማቲክስ ማስተማር ምንም ትርጉም የለውም ምክንያቱ ሊጠቀሙበት ስለማይችሉ ። :lol:

    ኣንድ የ ኦርዲናሪ ዲፈረንሻል ኢኰሽን ፕሮፈሰር ተማሪዎችን ለክቸር በመስጠት ኢያለ እንዲህ ብሎ ተናገረ ፥ እዚህ ተምረህ ልትስራ ስትሄድ የምትሰራበትን ኢኰሽን መስርያ-ቤትህን የሚሰጠህ እንዳይመስልህ ፡ በራስህን ነው የምታዘጋጀው ። :lol: :lol:

Re: ኣሁን ከድሉ ጎን ለጎን ትምህርት መሰረት ያደረገ የኢትዮጵያ ዳግመ-ትንሳኤ መመስረት ኣለበት። በነጮች የምትናቀውና የምትገደለው ዘመናዊ እውቀት የራስህን ስላላደረግህ ነው።

Posted: 01 Jan 2022, 16:36
by Abe Abraham
  • እውቀት ትቅደም ኣቆርቋዥዋ ይውደም !!!! Well done PMAA and የተከበረች ከንቲባ ኣዳነች ኣበቤ !!!!