ሰሚ አጣን እንጂ ብለን ነበር ! የአማራ ክልል መንግሥት እጁን ሰጠ
Posted: 22 Dec 2021, 09:46
የትግላችን አቅጣጫ!
የትግራይ ወራሪ ሀይል ያደረሰብን ጥቃት መቸውም የሚረሳ አይደለም። በክንዳችን እየተፋለምነው ቢሆንም ጠላት ግን ማጥፋት ወይም ስጋት መሆን ከማይችልበት ደረጃ ለማድረስ አልተቻለም። በመሆኑም አሁን ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ግዚያትም የሁላችን ዝግጁነት ይጠይቃል።
በተመሳሳይ የደረሰብንን የሀብት ወድመት መልሰን ለመተካትና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መልሰን ለማቋቋም ሁላችንም እንዘጋጅ። ኢኮኖሚያችን ለማነቃቃት በምንችለው መንገድ ሁሉ ፈጥነን ርብርብ ካላደረግነ ከጦርነቱ በላይ የአማራ ህዝብ ለተራዘመ ግዜ እንደሚጎዳ ማወቅ ይኖርብናል።
በመሆኑም የተጀመረውን የመስኖ ልማት በማጠናከር የከተሞችን የቢዝነሰ አካባቢና የመሠረተ ልማት ስራወች በማፋጠን የስራ እድል መፍጠር ይኖርብናል። መጭ ባህላዊና የሀይማኖት በአላትን እንደ ምቹ አጋጣሚ ወስደን የተቀዛቀዙ ከተሞችን ማነቃቃት አለብን። ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና የህዝባችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት መሠጠት ይኖርበታል።
ለዚህ ደግሞ የተረጋጋ አካባቢና ማህበራዊ ህይወት ቅድመ ሁኔታ በመሆኑ ሁላችንም ከመንግስት ጎን ተሰልፈን ለድርድር ድጋፋችንን እንስጥ። ከላይ በተቀመጡ የትኩረት ነጥቦች የትግል አቅጣጫችን ከተቃኘ የደረሰብንን ጥፋት ፈጥነን ተቋቁመን ለክልላችን ህብረተሰብ የህይወት መሻሻል ብሩህ ተስፋን እናሳያለን።
ሁልግዜ ፍላጎቶቻችን ማሳካት እንደምንችል በስራና በተስፋ እንኑር።
ፈጣሪ ይርዳን!
( የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ )