Page 1 of 1

Lalibela

Posted: 20 Dec 2021, 04:30
by Noble Amhara

Re: Lalibela

Posted: 20 Dec 2021, 13:06
by Assegid S.
"ዶሮ ብታልም ጥሬዋን" ይላል የኣማርኛ ተረት። የበድኑ ብአዴን አውራ ላሊበላ ገብቶ ስለጠፋው የሰው ልጅ ህይወት፣ ሰለተደፈሩት እናትና ሴት እህቶቻችን፣ ስለጎደለው የወንድሞቻችን አካል ግድ ሳይለው፤ ህወሃት አርዶ ስለበላው በሬ አማሮ፣ ቆፍሮ ስላወጣው ድንች ተቆጭቶ ተመለሰ። አይ ! ብአዴን … መች ይሆን ማተብህን እንደ ቀበቶ ከሆድህ ላይ ማሰሩን የምትተወው? መች ይሆን ሳታኝክ ለምትውጠው የከብት ሥጋ ሳይሆን ... ሳይበላ ላበላህ ህብረተሰብ ህይወት ዋጋ መስጠት የምትጀምረው?

መች በዚህ ብቻ አበቃ ይሔ እምብርት የለሽ … ሆደ-ቦሀቃ፤ ይግረምህ ብሎኝ ነው መሰለኝ ... ለወራት በህወሃት የጭካኔ ጅራፍ ሲያዠልጠው ለከረመው ምስኪን ወሎዬም "አይዞአችሁ የሚመጣው ገና ከነ ሙሉ ዝክሩ እዚሁ ይከበራል" ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃል ሲገባ ሰማሁት። ወሎ እንደሆን በሬው አልቋል … እንደትላቱ ገበሬውን አሳርዶ ከዘኬው መሐል ካልተሰየመ በስተቀር። የኣውሬ ሰው … የሰው ኣውሬ!