Page 1 of 1
ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 17 Dec 2021, 11:43
by Horus
ኢትዮጵያ የአለም ቅርስና ውርስ ነች፤ ለምን?
ዛሬ ሰው የምንለው እንሰሳ ዱር ከሚኖር እንሰሳነት ወደ ሰውነት የተለወጠው በኢትዮጵያ ነው። ሰው የተፈጠረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። በኢሪት ዘፍጥረት የተተረከው የአለም ታሪክ ወይም ተረክት የሆነው በኢትዮጵያ ምድር ነው። ዛሬ በገነነው የአርኪኦሎጂም (መሰረተ ምርምር) እና አንትሮፖሎጂ (የሰው ምርምር) ይህን ሃቅ አረጋግጦ ምስክሯ ብርቄ ወይም ሉሲ መሃላችን አለች ። በነገራችን ላይ ሉሲ ማለት ብርሃን ማለት ነው። ኢትዮጵያ የብርሃን አገር ነች ።
ዛሬ በብዙ በምዕራባዊያን ብዙ የሚንቆላጰሰው ሆሞ ሴፒየን ወይም የሚያስብ ሰው የሚለው ቃል እራሱ እኛ ኢትዮጵያዊያን ሰብ፣ ሰው ብለን ለአለም ሁሉ የሰጠነው ቅርስና ውርስ ነው ። ማለትም ...
ሰው የተፈጠረው (ኦሪተ ሰብዕ) በኢትዮጵያ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ቋንቋ የተፈጠረው በኢትዮጵያ ነው ። የመጀመሪያ የሰው ቋንቋ (ሂውማን ላንጉጅ) የተናገሩት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ። ዛሬ የምዕራ ቁንቋ ሊቃውንት ከዚህም ከዚያ ለቃቅመው ኢንዶ ኢሮፒያዊ የሚሉትና የእሱም አባት የሆነው አፍሮ ኤሲያዊ የሚባለው የአለም ቋንቋዎች ሁሉ አባል መገኛው ኢትዮጵያ ሲሆን መባል ያለበት አፍሮ ኤሲያን ሳይሆን ኢትዮጲክ ወይም ኢትዮጵያዊ ነው ።
ዛሬ የአውሮፓ ቋንቋዎች አባት የሚባለው ላቲን እራሱ ከሞላ ጎደል ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተቀዳ ነው ። ለዚህ ደሞ በቂ ማረጋገጫ ኤቪደንስ እየተከማቸ ነው። በመሆኑም ዛሬ በመላ ህንድ፣ ቅርብ ምስራቅ እና አውሮፓ ተሰራጭቶ ያለው የሉት የሴም ቋንቋዎች ሁሉ የተወለዱት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ።
የሰው ልጅ የመጀመሪያው ስልጣኔ በዋሻ መኖሩና እሳት መፈልሰፉ አይደለም፣ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ስልጣኔ ቋንቋ መፍጠሩ ነው። የስልጣኔ መጀመሪያ ቋንቋ ነው ። ይህን ስልጣኔ ለአለም የሰጡት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ።
በአንድ ቃል የስልጣኔ መጀመሪያ ኢትዮጵያ ናት፣ ይህ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ነው ወደ ጥንታዊ ግብጽ፣ ጥንታዊ ቅርብ ምስራቅና የህንድ አህጉር የተሰራጨው።
ሌላው ቀርቶ ዛሬ ብዙ ብዙ የሚባልለት የግሪክ ስልጣኔ በቅኝ ከተያዘችው ግብጽ ቤተ መዘክር የተዘረፈ እውቀት ነው ። ይህም ዛሬ በብዙ ሳንንሳዊ ምርምሮች እየተረጋገጠ ነው ። ዛሬ ማህበረሰብ ማደራጃ ፊሎሲፊ፣ ቲኦሪና ስልት የተባሉት እነዲሞክራሲ፣ ትምህርት፣ ወዘተ የሰው ልጅ ከኢትዮያ ጀምሮ እስከ ግብጽ፣ ህንድ፣ ሱመሪያ ወዘተ ያካበታቸው የሺዎች ዘመናት ስልጣኔ ክምችት እንጂ አንድ ቀን ሁለት ሶስት ግሪኮች ከሰማየ ሰማያት ያገኙት እውቀት አይደለም ።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ምሁራን አይናቸውን ገልጸው ያለም ቅኝ ገዦች የሚመግቧቸውን ዉሸት አስወግደው እውነትን ማየት መጀምሪያ ግዜው ዛሬ ነው!
በአ (ሆረስ ዘ ብሄረ ኢትዮጵያ)
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 19 Dec 2021, 22:14
by Horus
ታዲያ በዚህ በያዝነው 21ኝ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵይ ስልጣኔምን ይመስላል? በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ያለንበት የዕድገት ደረጃ የሚለካው እንዴት ነው? የአንድ አገር፣ የአንድ ህዝብ፣ ስልጣኔ መለኪያዎች ምንድን ናቸው? ዛሬ በዚህ የታሪክ ወቅት ኢትዮጵያን እየገዙ ያሉት ጥቂት ትላልቅ ሃስቦች ምንድን ናቸው?
አንድ፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት፣ ብሄረ አገር ጥንካሬና መንግስታዊ መረጋጋት በምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የሕዝብ አንድነት፣ ያገር ጥንካሬና የመንግስት መጽናት የሚለኩት እንዴት ነው?
ሁለት፣
የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህበራዊ መልካም አስተዳደር ስርዓት፣ ነጻነት፣ ፍትህና እኩልነት ህሳቤ፣ እድገትና ትግበራ ምን ይመስላል? ከምን ድረጃ ሰርሷል? መልካም አስተዳድር፣ ነጻነት፣ ፍትህና እኩልነት የሚለኩት እንዴት ነው? በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ምን ምን አይነት ያስተዳደር፣ የነጻነት፣ የፍትህና እኩልነት ፍልስፍናዎች አሉ? የተኞቹ ናቸው ገዢናተጽ ዕኖ ፈጣሪዎቹ?
ሶስት፣
የኢትዮዖያ ሕዝብ ብልጽግና ፣ ባለጸጋነት፣ ሃብታምነት፤ የትምህርትና ምሁርዊ፣ ሳይንሳዊን ቴክኖሎጂያዊ እድገት፣ ስፋት፣ ጥልቀትና ስርጭት ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ? የኢትዮጵያ ሕዝብ ጤንነቶች በየመስኩ ምን ደረጃ ይገኛሉ ? ችግሮቹ ምንድን ናቸው? ምን አይነት መፍትሄዎች አሉ?
አራት፣
ኢትዮጵያ ምን አይነት ካልቸር ነው ያላት? ፈጣሪ፣ ፈልሳፊ ካልቸር ምን ማለት ነው? የታሪክ፣ የአርት፣ ስለጽሁፍ፣ ሙዚቃና የጥበባት እድገታችን ምን ላይ ይገኛል? የኢትዮጵያ ኢኮሎጂያዊ ፍልስፍና ምንድን ነው? ኢትዮጵያዊያን ከከባቢያቸው ጋር ምን አይነት ዝምድና ነው ያላቸው? በእምነት፣ መንፈሳዊነት እና
የሕዝባችን ስነምግባራዊ እድገትና ጉድለት ምን ላይ ይገኛሉ? ዋና ዋና ችግሮቻችን ምንድን ናቸው? መፍትሄዎቹ ምንድን ናቸው?
በአ (ሆረስ ዘ ብሄረ ኢትዮጵያ)
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 19 Dec 2021, 23:15
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 19 Dec 2021, 23:57
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 20 Dec 2021, 02:46
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 20 Dec 2021, 03:02
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 20 Dec 2021, 23:24
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 21 Dec 2021, 00:53
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 22 Dec 2021, 03:41
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 22 Dec 2021, 04:47
by Horus
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 23 Dec 2021, 18:48
by Naga Tuma
ሆረስ፥
ስለ ሃገራችን የሰዉ ልጅ እና የስልጣኔ መጀመርያነት የፃፍከዉ ለወጥ ምርምር ኣቅጣጫ የያዘ ታሪካዊ ሰነድ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።
ከኣሁን በፊት ጠይቀን ያልተመለሱ ጥያቄዎችን የመለሰ። የኢትዮጵያ ታሪክ ከሙሴ በሁዋላ የተሰማ ብቻ ነዉ ወይስ ኣክናተን ሆኖ የኖረን እና ካዛ በፊት የነበረዉን ጊዜያት ይጨምራል? ከንግስት ሳባ ጉብኝት በሁዋላ የተሰማ ብቻ ነዉ ወይስ ከጉብኝቱ በፊት የነበረዉን ጊዜ ይጨምራል?
ይህ ታሪካዊ ሰነድ እንከን እንዲኖረዉ ኣልሻም። ተጨማሪ ከሆነ ያለኝን ሀሳብ ማካፈል እንጂ።
ቋንቋን መናገር መጀመር እና ምልክቶችን በመጠቃም መፃፍ መጀመር እንዳልከዉ እስከኣሁን በሰፊዉ ያልተዘካሩ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ቅርሶች ናቸዉ። ምናልባት ይህ ታሪካዊ ሰነድ የማይመልሰዉ ጥያቄ ካለ እስከኣሁን ኣልተመለሰም ተብሎ የሚታሰበዉ የሰዉ ልጅ መጀመርያ ኣንድ አከባቢ እና ኣንድ ወቅት ብቻ ነዉ ወይስ ብዙሃን ወይም ከኣንድ በላይ አከባቢዎች እና ወቅታት ናቸዉ የሚለዉ ይመስለኛል። ይህ ጥያቄ ደግሞ ወደ ሆሞስታሲስ ጥናት ልያመራን ይችላል። በዚህም ቢኬድ በእኔ መናሻ ጥናት ኣዲስ ኣበባ አከባቢ በዓለም ቀዳሚ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሰዉ ልጅ መጀመርያ አከባቢ ብዙሃን ሊሆን ይችላል ቢባልም ከሌሎች አከባቢዎች መቅደሙ ግን ኣከራካሪ ኣይመስለኝም።
ስለቋንቋ መናገር መጀመር ኣንትሮፖሎጂስት ባልሆንም ኣጥንቼ ለህትመት ላበቃዉ የቋጠርኩኝ ተምሳሌት ወይም ሞዴል ኣለ። በኤ ቡኤ፣ ባቴ ቡቴ ታምሳሌት ብዬ ሰይሜዋለሁ። ይህን ተምሳሌት መሰረት በማድረግ እና ተርታን ወይም ተሬን ወይም ፓተርንን በማስተዋል እና በማጥናት ለህትመት የሚበቃ ሳይንሳዊ ፅሑፍ መስራት የሚቻል የመስለኛል። ተርታዉን ባይጠብቅም በኤ ቡኤ፣ ባቴ ቡቴ ትርጉሙ ወጣ ወረደ፣ ወጣች ወረደች ማለት ነዉ።
ኣሁን እኔ ጋ ተቋጥሮ ከሚቀመጥ ተምሳሌቱን በመጠቀም ጥናቱን ለማሳካት ምኞት ያላቸዉ ኢትዮጵያዊያን ወይም ሌሎች ባለሙያዎች ካሉ ሀሳቡን ማካፈል ይሻላል ብዬ ኣሰብኩ።
ሁለተኛ፣ ቋንቋን ከመናገር መጀመርም በላይ ምልክቶችን በመጠቃም ቋንቋን መፃፈ መጀመር ምናልባትም ቆይቶ የመጣ ቢሆንም የበለጠ የታሪክ ቅርስ ሊሆን ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
እያንዳንዱ ቃል ታሪካዊ ብሎኬት ቢመሰል፣ እያንዳንዱ ፊደል ለብሎከቶቹ ማገር ወይም ሊሾ ሆኖ ሰብስቦ እንደቅርስ እንዳኖረ ሊመሰል ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
ለምሳሌ ሰሞኑን በእንግሊዘኛ ሬስ የሚለዉ ቃል በኢትዮጵያ ጎሳ ተብሎ በሰፊዉ ከሚታቀዉ ቃል የመጣ ይሆን ብዬ ሳስብ ቆይቼ ኣንዳንደ ነገሮችን ኣስተዋልኩኝ። ድምዳሜ ላይ ባያደርሱኝም ግምቴን ኣላላሉትም።
በታሪክ ገ እና ረ የተወራረሱበት ጊዜ ይኖር ይሆን ብዬ ሳስብ ኣንዱ ምልክት የሌላዉ ተገላብጦሽ ሆኖ ኣየሁት። ተጨማሪ ሳነብ ገ በኣንድ ወቅት ከላቲን ቋንቋ ፊደላት ከተወገዱ ጥቂት ፊደላት ዉስጥ መሆኑን ኣስተዋልኩ። ቀጥሎም በኣዲሱ እንግሊዘኛ ሬስ የተባለዉ ላቲን ቋንቋ ዉስጥ ራዛ ተብሎ ይታወቅ እንደነበረ ኣነበብኩኝ።
ታድያ የላቲን ቋንቋ ራሱ ከጥንታዊዉ የኢትዮጵያ ቋንቋ የወረደ ከሆነ ሬስ ተብሎ የሚታወቀዉ ቃል እኛ ጎሳ ብለን ከምናዉቀዉ ቃል ኣለመምጣቱን ማረጋገጥ ይቻላል? ኣይመስለኝም።
ስለዚህ ጥንት ጊዜ መናገሩን ከጀመርን፣ ጥንት ጊዜ መፃፉን ከጀመርን ዛሬ ደርሰን መዘከሩ እና ወደፊት ማሰደጉ ይቸገረን?
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 23 Dec 2021, 20:36
by Horus
ናጋ ቱማ፣
አው፣ ኢትዮጵያ የሰዉ ልጅ እና የስልጣኔ መጀመርያ ናት ያልኩት ትልቅ መደምደሚያ ሆነ ብዬ የወረወርኩት ። ጥያቄና ሃሳብ በሰዎች አይምሮ ውስጥ እንዲያጭር ነው። የድምዳሜው እርግጠኝነት ቀስ በቀስ ምርምር ይፈታዋል።
ስለሙሴም ሆነ ስለ ንግስተ ሳባ ያለው ታሪክ፣ ትርክት፣ ትውፊት፣ ሆነ ተረት (ተረክት) እውነተኛኑት የሚረጋገጠው በታሪክ። አርኪኦሎጂ፣ አንትሮፖሎጂ ምርመራና ፣ሌሎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ነው። ከዚያም ወደ ኋላ ሄደን ኢትዮጵያ ከጥንታዊ ግብጽ ጋር የነበራትት ትስስር ምን እንደ ነበር እንዲሁ በላይኞቹ ምርምሮችና በቁንቋ መረጃነት ይፈተሻሉ ማለት ነው። ያ እስከሚሆን ሁሉም ነገር መላምትና ያልተረጋገጠ ሃይፕቲሲስ ሆኖ ይቆያል።
የሰው ልጅ በዚህ ምድረ 200 መቶ ሺ አመት ኖሮዋል። ስለዚህ የሰው ቋንቋ ቢያንስ ያን ያህል እድሜ አለው ። የተጻፈ ቋንቋ ቢበዛ 10 ሺ አመታት አይበጥም ። አንድን ድምጽ ከሌላ ለይቶ (ፎነም) ያ ድምጽ (ቃል የምንለው) አንድ ሌላ ነገር እንዲያመለክት፣ እንዲወክል ማድረግ እጅግ ከፍተኛ ዲስከቨሪና እድገት ነበር። ይህ ሴማቲክስ የምንለው ነው ። የተለያዩ ሆሄያት፣ አናባቢዎችን አንተ እንዳልከው በመፍተል፣ በመሸመን (ሲንታክስ) እልፍ አይነት የተለያዩ ቃላት ማምረትም እንዲሁ የዚያ የቋንቋ ስልጠና አካል ነበር። ብሎም ፕራግማቲክስ የሚባለው ቋንቋ መተግበር ወይም ፕራክቲስ የማድረግ ሌላው የኮሚኒኬሽን ስልጣኔ ነበር ። ይህ ሁሉ ጽህፈት ከመጀምሩ በፊር የሆነ የኦራል ስልጣኔ ዘመን ነው። ስለ ተፈጥሮ ምስል መስራት ከጀመርን በኋላ ያየነውን ምሳል፣ የሰማነውን ድምጽ በምልክት መያዝና ማስቀመጥ ከተጀመረ ያለው ታሪክ ባብዛኛው የሚታወቅና የሚገኝ ነው። ሲጀመር የሰዕል ግራፍ ነበር፤ ከዚያም አብስትራክት ፊደላት መቅረጽ ተጀመረ ።
በመሰረቱ ግ ን አንድ ቃል ወይም ድምጽ ፣ የሚሰማ ብቻ ድምጽ (ዌቭ) ሆነ ወይ በአይን በሚታይ ምልክት ወይም የድምጽ ወኪል ስራቸው አንድ ነው፤ ድምጽ መያዝ፣ ማመልከት፣ ሃሳብ መያዝና ከሰው ሰው ማስተላለፍ ነው ።
ሰዎች ከኢትዮጵያ ወይም ከሽምጥ ሸለቆ ወጥቶ ከተሰራጨ በኋላ የቋንቋዎች ዝርያም በሺዎች ተራብቷል ተለያቷል። ጥንታዊ ስልጣኔዎችም ተራርቀም ተቀራርበውም በየአህጉሩ ተነስተው ነበር። ያም ሆኖ አልሁን ያለው ገዢ መደምደሚያ ያለም ቋንቋዎች ሁሉ ከአንድ እናት ቋንቋ የተራቡ ናቸው የሚል ነው ። ይህም ቋንቋ የመጀምሪያዎቹ የሰው ማህበሮች የተናገሩት መሆኑ ሎጂካል ነው። ወደፊት ይህ የሚረጋገጥ ነገር ነው ። የዘው ዘር ማፕ በጄኒቲክስ ተሰርቷል። ድምጽና ጄኔቲክስ ትስስር አላቸው ብዬ አምናለሁ ። የሌለን እንደ ሂዩማን ጂኖም ሂዩማን ፎነም ማፕ የሚያደርግ ሞዴል መፈልሰፍ ነው ፈተናው ።
በፊሎሎጂ ምርምርህ ቀጥል፣ የተረጋገጠ ነገር ስታገኝ በማጋራት አስተምረን ።
ሬስ ከሚለው ቃል አንድ ይሆነው ዘር የሚለው ነው ፣ ጎሳ የሚለው የተያያዘው ቤት፣ ጌይ፣ ገዛዕ ወይን ካሳ (እስፓኝ) ጋር ነው
ስለ ገ እና ረ ጥሩ አይተሃል (በፊደላት ቅርጽ መመሳሰል ማሰብ ማለት ነው) ድሮ በሂኒያርና ከዛ በፊር ሰማይ ወይም ራ እንደ ጋ ነበር የሚጻፈው ጋ ማለት ራ ማለት ነበር ፣ ገ እና ረ ተገለበጡ እንጂ ሲጸነሱ አንድ ነበሩ።
ይህ የሚያሳየው የሰው ልጅ ኢንተልክቿል እድገት ነው ። ድሮ የኮግኒሽናችን ችሎታ እንደ ህጻናት በነበረ ግዜ ወፍ ለማለት የወፍ ምስል ነበር የምንጠቀመው ቴክኖሎጂ፣ ከዚያ ከወፍ ቅርጽ ጋር ምንም የምይገናኝ ወፈ በፊደል ምክልት ተካነው ። ያም ቢሆን ፈ የወፍ አፍ ስለሚመስል በጣም አብስትራክት አይደለም። በማቲማቲክስ X = አለም፣ Y = ወፍ ወዘተ ስንል እጅግ በጣም ረቂቅ አብስርክሽን እንሰራለን ማለት ነው።
በአ ሆረስ፣ ዲሴምወር 23 2021
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 25 Dec 2021, 19:08
by Naga Tuma
ሆረስ፥
ኣመሰግናለሁ።
እኔ ስለ ማህበራዊ ሳይንስ ባለኝ ትርፍ ጊዜ የምማር እንጂ ሙያዉ ኖሮኝ ማስተማር የምችል ኣይዴለሁም።
ለዚህ ትንተና እና ቅርስ ተጨማሪ እንዲሆኑ ሁለት መጽሃፎችን ልጥቀስ። የመጀመርያዉ እ. ኣ. ኣ. በ1939 የታተመ Moses and Monotheism የሚል የስግመንድ ፍሪዩድ መጽሃፍ ነዉ።
ሁለተኛዉ እ. ኣ. ኣ. በ2002 የታተመ Moses and Akhenaten: The Secret History of Egypt at the Time of the Exodus የሚል የአህመድ ኦስማን መጽሃፍ ነዉ።
አህመድ አስማን የስግመንድ ፍሪዩድን ጥልቅ ጥናት ተቀብሎ የራሱን ሌላ ጥልቅ ጥናት ጨመረበት እንጂ ኣልነቀፈዉም፣ ኣልተካራከረዉም። አህመድ ኦስማን ተጨማሪ ጥልቅ ስራዉን ወደ ጥንቷ ኢትዮጵያ ወርዉሮ እስከኣሁን ተንጠልጥሎ ያለ ይመስለኛል።
የንተ ታሪካዊ ሰነድ ተንጠልጥሎ ያለዉን ለመፍታት ሰፊ በር የከፈተ መስሎ ነዉ የሚታየኝ። የሁለቱን ሊሂቃን ጥልቅ ምርመራዎች የምትነቅፍ ወይም የምትከራከር ኣይመስለኝም። ሁለቱም ጥልቅ ስራዎች መሰረታቸዉ የማይነቀፉ ወይም ኣከራካሪ ካልሆኑ የኢትዮጵያዊያን ሊሂቃኖች ቀጣይ ጥናት የተንጠለጠለዉን ታሪክ መሙላት እንጂ የተከናዉኑትን መንቀፍ ወይም መከራከር ኣይመስልኝም። የሚፈልጉም ካሉ ነቅፈዉ እና ተከራክረዉ ማሸናፍ ከቻሉ መንገዱ ለእናሱም ክፍት ነዉ።
ስለ ገ እና ረ በታሪክ ዉስጥ መወራረስ ኣላዉቅም ነበር። ስለጎሳ እና ዘር ልዩነት ከኣሁን በፊት እንደተወያየን ትዝ ይለኛል። በወቅቱ በርዕሱ ላይ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ሃይሌ የፃፉትን ኣካፍለህ ነበር፣ ካልዘነጋሁ።
ኣሁን ገ እና ረ በታሪክ ተወራርሰዉ የነበረ ከሆነ በኣጭሩ ዛሬ ሬስ የተባለዉ ምናልባት ጌስ ወይም ተመሳሳይ በሆነ ቃል የሚታወቅበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ማለት ነዉ። ኣይዴለም? ያ ማለት ደግሞ ሬስ የሚለዉን ቃል በጌስ ኣድርጎ ወደ ጎሳ ጠጋ ብያደርገዉ እንጂ ፈቀቅ ኣያደርገዉም።
ከሆነ የተለያየ ጎሳ የሆነዉን የሰዉ ልጅ ዘርን በዝርያ መከፋፈል መሠረት የለዉም ማለት ነዉ።
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 25 Dec 2021, 21:38
by Horus
ናጋ ቱማ፣ በፍሮይድና በአህመድ ኦስማን መሃል ስለ አንድ አምላክ እምነት የነበረው ክርክር አላውቀውም፤ የቲኦሎጂ ተማሪ ስላልኮንኩ የአንድ ጎድ እምነት ከአክነተን እስከ ሙሴ ያለው ታሪካዊ ፋክት ወይም ዋና ወይይታቸው ምን እንደ ነበር ትንሽ ጀባ ብትለን አናመሰግናለን
ስለ ዘርና ሬዝ በተመለከተ ያለው መመሳሰል ሁላቱ ቃላት ካልቸራል ኮንታክት እንደ ነበራቸው ነው ። አንዱ ያንዱ ቅጂ ነው ፣ ልዩነቱ አንዱ የሌላው ጉራማይሌ መህኖ ነው ። የነሱ ዝምድና ትርጉማቸው አንድ መሆኑ ነው ። የገና እና ረ ዝምድና የፊደሉ ቅርጽ ነው ።ጋ ራ ተብሎ ትርጉሙ ሰማይ ነበር ። ከጋ ወደ ራ ከተለወጠ በኋላ የጋ ትርጉም ስለማላውቀው ሰማይ ነው ለማለት አልችልም ። በትርጉም አንድ የሆኑ ቃላት በአንድ ካልቸር ወይም ቋንቋ ውስጥ የኖሩ ናቸው ። ያ ለመሆኑ ፋክት ያስፈልጋል ። ፊደል የቀረጹ ሰዎች ግን ከዚም ከዛም ዲዛይን ወስደዋል ።
በተረፈ ሰው አንድን ነገር ቁሳዊም ሆነ ጽንሳዊ፣ ጭብጥም ሆነ ምናብ (መና አብ) በፈለገው ስምና ምልክት ሊሰምና ሊያመለክት ይችላል ። ድሮ ግን ስም (ፎርም) ከነገሩ (ኮንቴንቱ) ጋር በምስልም በቁም ነገርም አንድ አንዲሆኑ ይሞከር ነበር ። ለምሳሌ እሳተ ጎመራን በረዶ ብለን አለመሰየም ማለት ነው ። እሳትና በረዶን ነክተው የሚያውቁ ሰዎች ሁለቱን በተሳሳይ ድምጽ አይጠሯቸውም ። ትርጉም ሴንስ ፐርሰፕሽን እና ከስሜት ጋር ስለተያያዘ ማለት ነው ። ዛሬ ከዳይረክት ኤክስፔሪያንስ ወደ መና አባዊ ሃሳብ እንዴት እንደ ምንሄድ ይታወቃል።
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 26 Dec 2021, 00:55
by Naga Tuma
ሆረስ፥
የስግመንድ ፍሪዩድም የአህመድ ኦስማንም መፃህፍት ካነበብኩ ቆይቻለሁ። ስለዚህ የማስታዉሳቸዉን ጭብጥ ሀሳቦች ላካፍል። የዘነጋሁት ወይም ሳነባቸዉ ሳይገቡኝ የተሳሳትኩ ካለ ሁለቱንም ሊህቃን ከዉዲሁ ይቅርታ በመጠየቅ ነዉ።
እኔ እንደገባኝ ከሆነ በሁለቱ መሃል ስምምነት እንጂ መሠረታዊ ክርክር የለም። የሁለቱም ስራ ጥንታዊ ታሪክ ላይ ያተኮረ ነዉ።
የስግመንድ ፍሪዩድ ዋና ነጥብ ሙሴ ወደ እስራኤል የሸሸ የግብጽ ፈረኦን የነበረ እንጂ እስራኤላዊ ኣልነበረም የሚል ነዉ። በዚህም ምክንያት እስራኤላዉያን የተመረጡ ህዝብ የሚለዉን ሀሳብ እሱ ከግብጽ የሸሸ ጊዜ የመረጣቸዉ እንጂ የእስራኤል ህዝብ እግዝኣብሔር መርጦናል ኣላሉም ይላል። መፅሃፉ የታተመዉ እ. ኣ. ኣ. በ1939 በጀርመን ሃገር ነዉ። በዛን ዓመት በዛ ሃገር እንደዚህ ዓይነት ሀሳብ ለመታተሙ መላምቶች ሊኖሩ ይችላሉ።
ሀሳቡን የሚደግፉ በዉል የማስታዉሳቸዉ ኣንደኛ የእስራኤል ህዝብ ሙሴ ወደ እነሱ ሳይሸሽ በፊት ያምኑ የነበረዉ በያዌህ ነበር ይላል። እሱ ከደረሰ በሁዋላ ተቀየረ ይላል።
ሁለተኛዉ የእስራኤል ህዝብ ከዛ በፊት ግርዛትን ኣያዉቅም ነበር። እሱ ነዉ ያስጀመራቸው ይላል።
አህመድ ኦስማን ስግመንድ ፍሪዩድ ሙሴ የግብጽ ፈረኦን የነበረ ነዉ የሚለዉን ትክክል ነዉ ብሎ ያ ፈረኦን የትኛዉ እንደነበረ ያስቀምጣል። ልብ በል። ስግመንድ ፍሪዩድ የትኛዉ ፈረኦን እንደነበረ ኣልፃፈም፣ ካልዘነጋሁ።
የአህመድ ኦስማን ዋና ነጥብ ስግመንድ ፍሪዩድ የስቀመጠዉ ፈረኦን አክናተን መሆኑን ማስቀመጥ ነዉ።
ለዚህም ግብዕ ዉስጥ ፈረኦን ሆኖ መምራቱን፣ ካዛም ወርዶ ወደ ጥንቷ ኢትዮጵያ መሸሹን፣ ከዛም ዐመጽ ተነስቶበት መሸሹን ይተነትናል።
ግብዕ ዉስጥ አክናተን የመጀመርያዉ ሞኖቴይስት መሆኑ የምያከራክር ኣይዴሌም። ለዛ አክናተን የሚለዉ ስም ብቻ በቂ ነዉ። ጣኦታትን ኣስትቶ በፀሃይ ያመነ፣ ያሳመነ ማለት ነዉ። ይህን ታሪክ ለማስረዳት አህመድ ኦስማን ብዙ መልፋቱን ኣላስታዉስም። ስግመንድ ፍሪዩድ ያለዉ ፈረኦን በልጅነቱ ስለኣንድ እግዝኣብሔር እምነት ኢትዮጵያዊት ከነበርችዉ እናቱ መማሩን፣ ከዛም ፈረኦን ሆኖ ማስተማሩን ነዉ።
ይህ ማስታወሻ ብዙ ጥያቄዎችን ባይመልስም መሠራታዊ ነጥቦችን እንዳስቀመጠ ኣስበለሁ።
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 26 Dec 2021, 04:57
by Horus
ይህ ጉዳይ እንደ ምታውቀው ዝብርቅርቅ ያለ ለብዙ ሺ ዘመን በቃል የተነገረ ስለሆነ በታሪኩና በትረቱ መሃል መለየት ከባድ ነው ። ሆኖም እኔ የማምነው የሙሴ ትርክት አላምነውም ። ሙሴ ልጅ ማለት ነው ። በግብጽ የረጅም ዘመን ተረት/ሚትዝ አለ አባይ ላይ በኬሽ ተጠቅልሎ ስለተጣለ ልጅ ወዘተ ስለዚህ የሙሴ ትርክት ከዚህ የግብጽ ሚቶሎጂ የተቀመረ ነው ።
ስለያዌ ያለው ትክክል ነው ግ ን የቃሉ ስር እብራስጥ ሳይሆን ኮፕቲክ ነው ። በጥንት የግብጽ ቃል ያ (Yah) ማለት ጨረቃ ፣ የጨረቃ ብርሃን ማለት ነበር። ስለዚህ ያዌህ ታመኑ የጨረቃ አምላኪዎች ነበሩ ። ይሁዶች ግብጽ ውስጥ ያዌን ማምለካቸው አያስገርምም ፣
Re: ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅና የስልጣኔ መጀመሪያ
Posted: 30 Dec 2021, 05:09
by Naga Tuma
Horus wrote: ↑26 Dec 2021, 04:57
ይህ ጉዳይ እንደ ምታውቀው ዝብርቅርቅ ያለ ለብዙ ሺ ዘመን በቃል የተነገረ ስለሆነ በታሪኩና በትረቱ መሃል መለየት ከባድ ነው ። ሆኖም እኔ የማምነው የሙሴ ትርክት አላምነውም ። ሙሴ ልጅ ማለት ነው ። በግብጽ የረጅም ዘመን ተረት/ሚትዝ አለ አባይ ላይ በኬሽ ተጠቅልሎ ስለተጣለ ልጅ ወዘተ ስለዚህ የሙሴ ትርክት ከዚህ የግብጽ ሚቶሎጂ የተቀመረ ነው ።
ስለያዌ ያለው ትክክል ነው ግ ን የቃሉ ስር እብራስጥ ሳይሆን ኮፕቲክ ነው ። በጥንት የግብጽ ቃል ያ (Yah) ማለት ጨረቃ ፣ የጨረቃ ብርሃን ማለት ነበር። ስለዚህ ያዌህ ታመኑ የጨረቃ አምላኪዎች ነበሩ ። ይሁዶች ግብጽ ውስጥ ያዌን ማምለካቸው አያስገርምም ፣
ሆረስ፥
እኔ ሳነባቸዉ ሁለቱም መፅሃፎች በቂ ማስረጃ ወይም ኤቪደንስ ያስቀመጡ መስለዉ ነዉ የታዩኝ። ፀሃፊዎቹ ብዙ ማስረጃዎችን ነዉ ያስቀመጡት። እያንዳንዱን ማስረጃ በሌላ ማስረጃ መደገፍ ወይም ኣለመደገፍ ይቻላል።
ብላክ አቴና ዉስጥ የተመዘገቡ ማስረጃዎች ያማይካዱ ከሆነ እነዚህ መፅሃፎች ዉስጥ ያሉ ማስረጃዎችም በቀላሉ የሚካዱ ኣይመስለኝም። የስግመንድ ፍሪዩድ መፅሃፍ ዉስጥ ከተቀመጡት ማስረጃዎች ዉስጥ ያዌ እና ግርዛት እንዴት ተቀምጠዉ ተመዘዉ ወጡ ብዬ ገርመዉኛል። ሙሴ ትርጉሙ ልጅ ቢሆንም ከሃይሮግልፍክ እስከ ቶራ እና ሙጫ ያሉት ጥንታዊነቱን እና ምናልባትም የጥንታዊት ግብፅ፣ ጥንታዊት ኢትዮጵያ፣ እና ጥንታዊት እስራኤል መሪ የነበረ መሆኑን ያማይደግፉ ኣይመስለኝም።
ያዌ፣ ዋቀ፣ እና ሌሎች ተመሳሳይ ቃላት እስከ እሩቅ ምስራቅ ድረስ ተመሳሳይ የሆኑ የጥንት ቃላት መሆናቸዉን ፈረንሳዩ ዲ ሳልቪያ የተባላ እ. ኣ. ኣ. በ1901 ባሳተመዉ መፅሃፍ ዉስጥ ኣስቀምጧል።