ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ንብረቶችን በማጓጓዝ ላይ መሆኑን ተከትሎ በምእራብ ወረዳ ተደራጅተው የሚጠብቁ ወጣቶች "ለምን?" ብለው ሲጠይቁ አይ "ይህ የአካባቢው ነዋሪ ንብረት ሳይሆን አሸባሪው ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ ጥሎት የሸሸውነው" የሚል የሽንገላ ቃል እየተናገሩ ይገኛል።
እንኳን በመረጃና በማስረጃ የባለቤትነት ፍቃድ እያሳዩ የተዘረፈው ቀርቶ እንዳሉትም የአሸባሪው ቡድን ንብረት ቢሆን በአደራ አካባቢው ላይ ተቀምጦ መንግስታዊ በሆነ አካል ተጣርቶ የግለሰብም ከሆነ ለግለሰብ፣ የመንግስትም ከሆነ ለመንግሥት ይመለሳል እንጅ እንዴት ወሮ በላ ይጓጉዘዋል?!
የሆነ ሆኖ የአሸባሪው ቡድን ቢሆን ራሱ ከየት እንዳመጣውና ከየት ዘርፎ ሲጠቀምበት እንደነበረ ግልፅ ነው። ስለሆነም የመንግስት አካል ይህን አውቁ ሊያስቆም ይገባል። ከዛ ውጭ ስንት ጀግናና በሚሊዮን የሚቆጠር ሀብት ንብረት እያለው ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት በዘመተ ፋኖ ስም መነገድ ከወንጀልም በላይ ዓይን ያወጣ ስርአት አልበኝነት ነው።
ሲቀጥል ማንም ይሁን ማን ሌባ- ሌባ ነው! በብሔር፣ በሀይማኖት፣ በአርበኝነትም ሆነ በሌላ በምንም ዐይነት አመሃኝቶ መዝረፍ ሌባ ከመባል አያስመልጠውም።
ለመሳ መሳማ አሉ!! ህዝቡን ከዘረፋችሁ ካሰቃያችሁ እውነት እናንተ ከአሸባሪው ቡድን በቋንቋ ካልሆነ በምን ተለያችሁ ምግባራችሁ የብዙዎችን ተጋድሎና ዋጋ እንደሚያሳንስም ልብ ልትሉ ይገባል።
Please wait, video is loading...




