Reyot Alemu & Teborne Beyene left Ethio 360. Guess who will leave Ethio 360 next?
Posted: 11 Dec 2021, 21:20
ፍቺ!
ርዕዮት ዓለሙና ተቦርነ በየነ፥ ከኤርምያሰ ለገሰና ሃብታሙ አያሌው ጋር የፈጸሙት ፍች ይፋ ሆነ።
የርዕዮትና ተቦርነ መግለጫ ከዚህ በታች
ሰላም ለሁላችሁም
በሀገራ ችን የመጣውን አንፃራዊ የፓለቲካ ለውጥ ተከትሎ እንሰራበት የነበረው የኢሳት ሚዲያ ውስጥ በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ከኢሳት ወጥተን ኢትዮ 360 ሚዲያን ከሌሎች አብረውን ይሰሩ ከነበሩ ባልደረቦቻችን ጋር ከህዝብ ባገኝነው ከፍተኛ ድጋፍ ማቋቋማችን ይታወቃል።
ሆኖም በሚዲያው መስራች አባላት መሀከል ያለው የፍላጎት፣የአካሄድ፣እና ሌሎች ልዩነቶች እየሰፉ በመምጣታቸው እንዲሁም ለማስተካከል የተደረጉ ሙከራዎች ባለመሳካታቸው በጋራ እንሰራበት የነበረውን ፕሮግራም በመተው በየግላችን በምናዘጋጃቸው መደበኛ ፕሮግራሞች እና ለሁለት በምናዘጋጀው ልዩ ፕሮግራም ተወስነን ቆይተናል።
በኢትዮ 360 ሚዲያ ላይ የምናቀርባቸውን ፕሮግራሞች ሙሉ ለሙሉ አቋርጦ በሌላ የዩትዩብ ቻናል ስራችንን መቀጠሉ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘነው ምንጊዜም ሚዲያ ~Mengizem Media በተሰኘ የዩትዩብ ቻናል እና የፌስቡክ ገፅ ከዛሬ ሀሙስ ህዳር 30,2014 አ.ም(December 9,2021) ጀምሮ ፕሮግራሞቻችንን ማቅረብ የምንቀጥል መሆኑን እናሳውቃለን።
ከምስጋና ጋር
ተወልደ በየነ(ተቦርነ)
ርዕዮት አለሙ
https://www.facebook.com/bekele.daniel. ... 7479948125