Page 1 of 1

ኣሁን ደሞ የሻብያ ተራ በእጅ ኣዙር ግዛት?

Posted: 11 Dec 2021, 18:56
by ethiopianunity
እንደምናውቀው፣ ኢትዮዽያን ለማንበርከክ ነጻውጪዎች በኤርትራ ነጻውጪዎች መሪነት ኢትዮዽያን ያዙ። ግን ቃልኪዳናቸው ከሾሟቸው የመካከለኛው ምስራቆችና ምራባውያን ቡድኖች ነው። ህዋሃት ኣንደኛው ወድሞ ኣሁን ደሞ ሻብያ ሁለተኛው ህዋሃት ሆኖ ጦርነቱ እስከሚፈለገው ድረስ ማናልባትም ኢትዮዽያን እስከማፍረስ ወይም እስከሙሉ ለሙሉ እስመቆጣጠር ድረስ ህውሃት ኣንደኛው እንዳደረገው። የውጭ ሃይሎቹ ጦርነቱን እያፏፏሙ ያሉት ኣባይንና ተፈጥሮ ሃብትን ከመቆጣጠር በላይ ኣፋር፣ትግራይንና ኣማራን ኣጥፍቶ የራሳቸውን ኣማልክት ለማቋቋም ነው። ይህን ለማድረግ የሚያስችል መሳርያ የሆኑት ሻብያ፣ ህዋሃትና ኦነግ ናቸው። ጉልቻ ቢቀያየት ወጥ ኣያጣፍጥም እንደተባለው ህውሃት ቢሄድ፣ ሻብያ ሁለተኛውን ህዋሃት ሆኖ ሳይመጣ ኣይቀርም። ግን በትግራይ ስም ነው የሚንቀሳቀሰው ያው የኢትዮዽያ ህዝቦች በተለይም ኣማርውና ትግራዩ እስከሚላላቁ ድረስ። ለጊዜው ደግሞ ኦነግ ህዋሃትን ስለሚተካ ኣዲስ ኣበባ፣ በደስታ ፈንጥዞ ኣርቆ ማሰብ ስለማይችል ይህን ኣደጋ ኣይመለከትም ከመጀመርያው ህዋሃትም ኣይማርም።