Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37253
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ዕቃ ይዘው የነበሩ 251 ኮንተይነሮችን ዘርፏል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 10 Dec 2021, 12:46

Please wait, video is loading...
አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ዕቃ ይዘው የነበሩ 251 ኮንተይነሮችን ዘርፏል
****************
(ኢ ፕ ድ)

አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ የደንበኛ እቃ ይዘው ተከማችተው የነበሩ 251 ኮንተይነሮችን ሙሉ ለሙሉ መዝረፉንና ማውደሙን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ።

የድርጅቱ የወደብና ተርሚናል አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረተአብ ተክሉ በሰጡት መግለጫ የወደቡ እቃ በአሸባሪው ህወሃት በሙሉ ዘረፋና ውድመት ተፈፅሞበታል ብለዋል።

በአራት ሔክታር መሬት ላይ የተገነባው የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ በወቅቱ 251 የደንበኞችን እቃ የያዙ ኮንተይነሮች የነበሩት ሲሆን በአካባቢው ወረራ የፈፀመው አሸባሪ ሃይል ሙሉ ለሙሉ ዘርፎታል፤ ያልቻለውን ደግሞ አውድሞታል ብለዋል።

ኮንተይነሮቹ የኢንዳስትሪ ግብዓቶች፣ ማሽነሪዎች፣ ምግብና መድሃኒቶች እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዙ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ ሁሉም ንብረቶች በአሸባሪው ህወሃት መዘረፋቸውን አቶ ምህረተአብ ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ በአመት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝና ለበርካቶች የስራ እድል የፈጠረና ለአገሪቷ ትልቅ የኢኮኖሚ ፋይዳ ያለው እንደነበርም ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የገቢና የወጪ እቃዎች ከሚንቀሳቀሱበት ወደቦች መካከል የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ አንዱ እንደነበርም አንስተዋል።

አሸባሪው ህወሃት በወደቡ ላይ ያደረሰውን ውድመት በተመለከተ በቀጣይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዝርዝር መረጃ እንደሚቀርብ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከሚያስተዳድራቸው 8 ደረቅ ወደቦች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

አካባቢህን ጠብቅ‼
ወደ ግንባር ዝመት‼
ሠራዊቱን ደግፍ‼

ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ 👇
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም 👇
https://t.me/ethpress
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ 👇
https://www.press.et/