20ffa5a2sr5c2g236ch ·
"የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው እያሉ
አሸባሪው ህወሓትን እየሞገቱ ነው"
- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት
ሚኒስትር
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የትግራይ እናቶች ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው እያሉ አሸባሪው ህወሓትን እየሞገቱ ነው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ የሽብር ቡድኑ በትግራይ እናቶች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን አሰመልክተው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የትግራይ እናቶች በአሸባሪው ህወሓት ስብሰባዎች ላይ አንገኝም እያሉ ነው።
ተገደው የተገኙትም ልጆቻችንን የት አደረሳችኋቸው ብለው እየሞገቱ ነው። በዚህም ምክንያት አሸባሪው ቡድን ሕዝባዊ ቁጣ ተነስቶበታል ብለዋል።
አሸባሪዎቹም እርስ በእርሳቸው መናቆር አብዝተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የአሸባሪው ቡድን ግብዓተ መሬት ሩቅ እንዳልሆነ ያሳያል ብለዋል።
ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፤ ተላላኪው ሸኔ ላይ አስፈላጊው እርምጃ እየተወሰደ ነው፤ እርምጃውም ይቀጥላል ብለዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም
አካባቢህን ጠብቅ‼
ወደ ግንባር ዝመት‼
ሠራዊቱን ደግፍ‼
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን ‼
ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም
https://t.me/ethpress
ትዊተር
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ
https://www.press.et/

