Page 1 of 1

ሰበር ዜና:ሓይቅ፣ ውጫሌ፣ ቢስቲማ ጎሽ ሜዳና ሌሎች በርካታ ቦታዎች ነጻ ወጡ!!!!!

Posted: 08 Dec 2021, 15:19
by Ejersa

Re: ሰበር ዜና:ሓይቅ፣ ውጫሌ፣ ቢስቲማ ጎሽ ሜዳና ሌሎች በርካታ ቦታዎች ነጻ ወጡ!!!!!

Posted: 08 Dec 2021, 15:22
by Hameddibewoyane
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል
Ejersa wrote:
08 Dec 2021, 15:19

Re: ሰበር ዜና:ሓይቅ፣ ውጫሌ፣ ቢስቲማ ጎሽ ሜዳና ሌሎች በርካታ ቦታዎች ነጻ ወጡ!!!!!

Posted: 08 Dec 2021, 15:41
by Ejersa
በአሸባሪው ህወሓት ተወረው የነበሩ ቀሪ ከተሞች በጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ እየወጡ ነው።

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ሕወሓት ተወርረው የነበሩት ቀሪ ከተሞች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በ “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በወሰዱት ማጥቃት ነጻ እየወጡ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ንጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶ ሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል።

ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ መሆኑን ነው የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያስታወቀው።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽ ሜዳ ከአሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ነጻ መውጣታቸውንም ገልጿል።

በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደ ውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት ይገኛሉ።