Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 37251
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

♤♤♤{{{BREAKING NEWS}}}♤♤♤በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች፡ በተንታ ግንባር ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ነጻ ወጥተዋል!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 08 Dec 2021, 14:35

Please wait, video is loading...
ሰበር ዜና‼️

በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች፡ በተንታ ግንባር ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ነጻ ወጥተዋል።
************************
(ኢ ፕ ድ)

በአሸባሪው ሕወሐት ተወርረው የነበሩት ቀሪ ከተሞች፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ በዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በወሰዱት ማጥቃት ነጻ እየወጡ ነው።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ለኢፕድ በላከው መግለጫ ጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በደሴ ግንባር ሐይቅ፣ ቢስቲማ፣ ባሶሚሌ እና ውጫሌ ከተሞች ነጻ ወጥተዋል። ሠራዊቱም ወደ መርሳ እየገሠገሠ ነው።

በተንታ ግንባር በተካሄደው ማጥቃት ዓለም አምባ፣ መቅደላና ጎሽሜዳ ከአሸባሪው የሕወሐት ወራሪ ነጻ ወጥተዋል።

በሁሉም ግንባሮች የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ወደውስጥ ዘልቀው በመግባት የተበታተነውን አሸባሪ ኃይል ቀለበት ውስጥ አስገብተው በመደምሰስ ፣ ወራሪው ኃይል የዘረፈውን ንብረት እንዲሁም የያዘውን መሣሪያና ትጥቅ ይዞ እንዳይወጣ እያደረጉት ይገኛሉ።