የ”በቃ” NoMore ንቅናቄ አሜሪካ “በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ስለመፈፀሙ የሚያትተውን አዋጅ እንድትሰርዝ አደረገ
Posted: 08 Dec 2021, 04:26
የ”በቃ” ንቅናቄ አሜሪካ “በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ስለመፈፀሙ የሚያትተውን አዋጅ እንድትሰርዝ አደረገ
**************************
የኢትዮጵያውያን እና የሌሎች የ”በቃ” የ ‘#NoMore’ ንቅናቄ የአሜሪካን ብሄራዊ መከላከያ ፍቃድ ህግ (NDAA) “በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል “የሚለውን ረቂቅ ህግ እንዲሰርዝ ማድረጉ ተገለጸ።
ይህ የሆነው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ዲያስፖራ አፍሪካዊያን እና መላው የ ‘#NoMore’ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ለአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ስልክ በመደወል ኢሜይል በመፃፍ እንዲሁም ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት ባደረጉት ከፍተኛ ተጋድሎ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህም የኢትዮ- አሜሪካን የልማት ምክር ቤት ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራዊያን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ባደረጉት የ #NoMore ንቅናቄ ተፅእኖ ምክንያት ረቂቅ አዋጁ ባለመፅደቁም ምስጋና አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያውን አሁን ላይ ባገኙት ድል ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ኢትዮጵያን የሚጎዱ ህጎችንእንዳይፀድቁ የአሁኑን ትብብር ማስቀጠል አለባቸው ብሏል ምክር ቤቱ ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጥምረት ባካሄዱት ጥናት ትግራይ ውስጥ የዘር ማጥፋት ተግባር አለመፈፀሙን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡
በተቃራኒዉ … የወያኔ ጁንታ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመዉን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከታች ባለዉ ቪዲዮ ይመልከቱ።