Page 1 of 1

በአሸባሪው ጁንታ ማኒፌስቶ መሰረት የተቋቋመው 16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ዋዜማ እየተከበረ ነው

Posted: 07 Dec 2021, 19:40
by sarcasm
16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ዋዜማ እየተከበረ ነው
ኅዳር 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) 16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦና ሕዝቦች ቀን በዓል ዋዜማ በድሬዳዋ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በዋዜማው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መአዛ አሸናፊን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ዋዜማው በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን በዛሬው እለትም በዓሉን አስመልክቶ በከተማው የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ተከፍቷል።
እንደ ዋልታ መረጃ ከሆነ አሁን ላይ ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ የብሔር፣ ብሔረሰቦያ ህዝቦች ተወካይ ልዑኮች በታደሙበት ልዩ አገራዊ የሙዚቃ እና የእራት ስነ ስርዓት በመካሔድ ላይ ይገኛል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በድሬዳዋ አስተዳደር በ32 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ መጎብኘታቸው ይታወሳል።
16ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች በድሬደዋ አስተናግጅነትይከበራል።
Please wait, video is loading...

Re: በአሸባሪው ጁንታ ማኒፌስቶ መሰረት የተቋቋመው 16ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ዋዜማ እየተከበረ ነው

Posted: 07 Dec 2021, 19:55
by Misraq
No rash, neftegna will dismantle that very soon. We can't do all things at once 😂