Page 1 of 1

ደሴ እና ኮምቦልቻ ነፃ ስለወጡ ፕሬዚዳንቷ ብሔራዊ በዓል አወጀች

Posted: 07 Dec 2021, 11:16
by Thomas H
እነዚህ ማፈሪያዎች 140 ሚሊዮን ሕዝብ ይዘው ሳይዋጉ የሰጠናቸውን ከተሞች እንደ ትልቅ ድል አድርገው ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል

ፕሬዚደንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ።
#Ethiopia : የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በርካታና ቁልፍ ከተሞች ነጻ እየወጡ ነው ያሉት ፕሬዚደንቷ "እንኳን ደስ አለን" ብለዋል፡፡







ገዱ አንዳርጋቸው
#Ethiopia : ክብርና ሞገስ ለጀግኖቻችን እና ለፈጣሪ!! በእነሱ መራር ተጋድሎና ክቡር መስዋእትነት ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞቻችን ነፃ ወጥተዋል። በወገኖቻችን ላይ መጠነ ሰፊ ግፍ ቢፈፀምም፣ንብረታችን ቢዘረፍም ከተሞቹን ጨምሮ አካባቢው ከፍተኛ ውድመት ቢደርስበትም ዋናው ጉዳይ ሰው ነፃ መሆኑ ነውና ህዝባችን ከነዚያ አውሬዎች በፈጣሪ ሃይል ነፃ ወጥቷል እንኳን ደስ አለን።

Re: ደሴ እና ኮምቦልቻ ነፃ ስለወጡ ፕሬዚዳንቷ ብሔራዊ በዓል አወጀች

Posted: 07 Dec 2021, 15:13
by Tadiyalehu
አይጥ ወያኔ!
ነገ ደግሞ መቀሌንም በፈቃዳችን ነው የለቀቅነው ማለታችሁ አይቀርም! :lol: :lol: