
ፕሬዚደንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ።
#Ethiopia : የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ በተገኘው ድል የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በርካታና ቁልፍ ከተሞች ነጻ እየወጡ ነው ያሉት ፕሬዚደንቷ "እንኳን ደስ አለን" ብለዋል፡፡

ገዱ አንዳርጋቸው
#Ethiopia : ክብርና ሞገስ ለጀግኖቻችን እና ለፈጣሪ!! በእነሱ መራር ተጋድሎና ክቡር መስዋእትነት ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞቻችን ነፃ ወጥተዋል። በወገኖቻችን ላይ መጠነ ሰፊ ግፍ ቢፈፀምም፣ንብረታችን ቢዘረፍም ከተሞቹን ጨምሮ አካባቢው ከፍተኛ ውድመት ቢደርስበትም ዋናው ጉዳይ ሰው ነፃ መሆኑ ነውና ህዝባችን ከነዚያ አውሬዎች በፈጣሪ ሃይል ነፃ ወጥቷል እንኳን ደስ አለን።