Page 1 of 1

ልደቱ አያሌው በእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢሳቅ እና በእነ ኢሌኒ ገምብረመድ በሚመራው የሽግግር መንግስት ምስረታ ጉብኤ ላይ ባለመገኘቱ ከልብ የሆነ ከባድ ይቅርታ ጠየቀ!!

Posted: 25 Nov 2021, 12:53
by Wedi
ልደቱ አያሌው በእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢሳቅ እና በእነ ኢሌኒ ገምብረመድ በሚመራው የሽግግር መንግስት ምስረታ ጉብኤ ላይ ባለመገኘቱ ከልብ የሆነ ከባድ ይቅርታ ጠየቀ!!

:lol: :lol: :lol: :P :P

ከልብ የሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ

በአምባሳደር ብርሃነ የተመራውና ወዳጆቼ ዶክተር እሌኒና ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና ሌሎች የቅርብ ወዳጆቼ በተሰበሰቡበት የሽግግር መንግስቱ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ የስብሰባው አባል ብሆንም ባለመገኘቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ ። ልገኝ ያልቻልኩበት ምክንያት ሌላ የሽግግር መንግስት በነያሬድ ጥበቡና በነታምራት ላይኔ ስለተቋቋሙና እሱ ውስጥ አባል ስለሆንኩኝ ነው ።

ቅዳሜ ደግሞ በነፕሮፌሰር ሕዝቅያስ የተመሰረተ ሌላ የሽግግር መንግስት ውስጥ በአባልነት ተሳትፌያለሁ ። እነሀብታሙ አያሌውም የእኛ የሽግግር መንግስት አባል ሁን እያሉኝ ነው ። እስካሁን ድረስ አስራ አምስት የተለያዩ ሽግግር መንግስቶች ውስጥ አባል ስለሆንኩ ጊዜ ሊበቃኝ አልቻለም ። እንደመፍተሄ የሽግግር መንግስቶቹን የሚያሸጋግር የሽግግሮች ሽግግር አሰባሳቢ በቅርቡ ሁላችሁንም እጠራችኋለሁ ።


Please wait, video is loading...