11m ·
በዴሞክራሲ ስም የሚፈጸመው ወንጀልና አገር ማፍረስ ሊበቃ ይገባል ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ
**************************
(ኢ ፕ ድ)
ቃል አቀባዩ ሚስተር ዋንግ ዌንቢን በማሀብራዊ ገጻቸው ላይ የኢትዮጵያዊያንን የበቃ (#Nomore) የተቃውሞ ዘመቻ ተቀላቅለዋል።
ቃል አቀባዩ በዚሁ መልዕክታቸው ላይ “በዴሞክራሲ ስም ምንያህል ወንጀል ተፈጸመ” ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ቃል አቀባዩ ለዚህ መልዕክታቸው የተጠቀሙት ምስልም ሰሞኑን በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለተቃውሞ ሲወጡ ይዘዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል አንዱን ሲሆን፤ በግልጽም ቃል አቀባዩ “#NOmore” ሲሉ ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል።
ቃል አቀባዩ የተጠቀሙት ምስልም አፍጋኒስታንን፣ ኢራቅን፣ የመንን እና ሶሪያን ፈርሰዋል ቀጣይዋ ተረኛ ኢትዮጵያ ናት ወይ ሲሉ ሰልፈኞቹ የአሜሪካን መንግስት የጠየቁበትን ነው።
በሀይማኖት ከበደ
አካባቢህን ጠብቅ ‼
ወደ ግንባር ዝመት ‼
ሠራዊቱን ደግፍ ‼
ተጨማሪ የመረጃ አማራጮቻችን
ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCoH2CVwWn9suWP7q0u2L7MA
ቴሌግራም
https://t.me/ethpress
ትዊተር
https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ
https://www.press.et/

