በዲያስፖራ የሚኖረው የኦሮሞው ማህበረበብ ከብልፅግና ጎን አለመሰለፉን ማሳያ
Posted: 22 Nov 2021, 08:53
በተለያዩ 27 የአለም ከተሞች ላይ ኢትዮጲያውያን ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደ መድሃኒት ጣል ጣል ብሎ ከሚታዬው የኢትዮጲያ ፌደራል ባንዲራ በስተቀር በስፋት የታዩት የአሃዳውያን እና የኤርትራውያን ባንዲራ ነው። በሰልፉ ላይ የፌዴራል ሀይሎች ነው ተብሎ የሚታሰበው ባንዲራ ካለመታየቱ ጎን ለጎን የአባ ገዳም ሆነ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ ፈፅሞ አልታየም። የኦሮሞ ማህበረሰብ ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ካልሆኑ በስተቀር ልሙጠን ባንዲራ ሊያውለበልቡ አይችሉም። ከዚህ የምንረዳው በዲያስፖራ የሚኖረው የኦሮሞው ማህበረበብ ከብልፅግና ጎን አለመሰለፉን ነው።
ይሄ ሆኖ ሳለ ግን በዲያስፖራ የሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ ያለውን አቀም ተጠቅሞ ለኦሮሞ ህዝብ ትግልም ሆነ በየእስርቤቱ ታጉረው ስለሚገኙት መሪዎቹ ድምፁን በአደባባይ ሲያሰማ ብዙም አይስተዋልም። በሀገር ውስጥ የሚገኙት የኦሮሞ እና የትግራይ ታጋዮች ባላቸው ሀገራዊ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ አንድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በጦርነት ግንባርም ለጋራ አላማ በጋራ ህይወታቸውን እየበገሩ ይገኛሉ። በዲያስፖራ የሚገኘውም የኦሮሞ እና የትግራይ እንዲሁም ሁሉም ፌዴራሊስት ማህበረሰብ ይሄን ትግል የሚደግፍ መሆኑን በተቀናጀ እና በተባበረ መንፈስ በተግባር ማሳየት መቻል አለበት። ይሄንን የምለው አሁን አሃዳውያን እያደረጉ ያሉት ሰልፍ በአለምአቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የኢትዮጲያ ህዝብ የብልፅግና ደጋፊ ነው የሚል ምስል እንዳይዝ ነው።
በተለይ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ ካለው ሀገራዊ የወሳኝነት ታላቅ ሚና አንፃር አቋሙን ለአለም ማህበረሰብ በግልፅ የሚያሳይበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ዝምታው ትግል ያዳክማል። ድጋፉ ታጋዮችን ያበረታል፣ አሃዳውያንን ያዳክማል። መሀል ቤት የቆመውንም ያነቃል።
Sarcasm's comment: በቀላል ትግርኛ፤ ሰልፉ የኣምሓሩና የሻዕብያ ነበር።

Please wait, video is loading...