Page 1 of 1

<<<(((JUST IN)))>>>በኣሸባሪ-ጁንታ ከደባርቅ ወደ ጎንደር ተጭኖ ሊወጣ የነበረ የጦር መሳሪያና ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 21 Nov 2021, 11:52
by tarik
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
11t41on19300o028t62utmi3e7 ·
ከደባርቅ ወደ ጎንደር ተጭኖ ሊወጣ የነበረ የጦር መሳሪያና ጥይት በቁጥጥር ስር ዋለ
*********************
(ኢ.ፕ.ድ)
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ባደረገው የተጠናከረ ክትትል ብዛቱ ከሰናት ሺህ በላይ የሆነ ተተኳሽ የብሬንና የክላሽ ጥይት፣ ክላሽን ኮቭ ጠብመንጃ፣ ልዩ ልዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፣ ሲም ካርዶች እና የብሬን አንገት በደባርቅ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በጎንደር ከተማ የቀበሌ 15 ነዋሪ የሆነው ፍጹም ገብረ ክርስቶስ በሰሌዳ ቁጥር 03 አማ - 25162 በሆነ ሚትስቡሽ ፒክ አፕ መኪና ለጸጥታ አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠሁ ነው በማለት በተከዜ ግንባር ከሳምንት በላይ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
ግለሰቡ ወደ ዛሪማ በሚመላለስበት ወቅት የወገንን ሃይል አሰላለፍና የከባድ መሳሪያዎችን አቀማመጥ ለጠላት መረጃ አሳልፎ ሲሰጥ እንደቆየና አሁንም በመኪናዋ ላይ ሞደፊክ ባሰራው የሕገ ወጥ እቃዎች መጫኛ ተተኳሾችን ከዛሪማና ከደባርቅ በመሰብሰብ ወደ ጎንደር ወስዶ ለቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ለማቀበል ስምምነት እንደነበረው መናገሩን የሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡