9h16thS16l6uanoeug ·
የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግ ጥረትን እንደሚቃመዉ ገለጹ!
የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቴሽኬዲ፤ በኢትዮጵያ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግ ጥረትን እንደሚያወግዙ አስታወቁ፡፡ፌሊክስ ቴሽኬዲ፤ የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ ምንም አይነት ድርድር እንደማያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ሊቀመንበሩ ይህንን ያሉት፤ በሀገራቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ክሪስቶፍ ሉቱንዱላ በኩል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሁም ከአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ ክሪስቶፍ ሉቱንዱላ ጋር በአዲስ አበባ ተወያተዋል፡፡አቶ ደመቀ እና ክሪስቶፍ ሉቱንዱላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና የአፍሪካ ህብረት የመፍትሄው አካል በመሆን ሊጫወቱት የሚችለውን ሚና በተመለከተ መወያየታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
