ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ የቱሪዝም ሥራ እጅግ በመጎዳቱ ግብር መክፈል ባለመቻላቸው የአስጎብኚ ድርጅቶች የባንክ ሒሳብ ታገደ (ሪፓርተር)
Posted: 20 Nov 2021, 09:08
የአስጎብኚ ድርጅቶች የባንክ ሒሳብ ታገደ
17 November 2021
በጋዜጣዉ ሪፓርተር
በአሸናፊ እንዳለ
የግብር መክፈያ ጊዜ በመጠናቀቁ ምክንያት ያለፈውን ዓመት ግብር መክፈል ባለመቻላቸው፣ የአስጎብኚ ድርጅቶች የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ ከሦስት ሳምንት ወዲህ መታገዱን የሪፖርተር ምንጮች አረጋገጡ፡፡
የአዲስ አበባ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ጽሕፈት ቤት መስከረም 15 ቀን 2014 ለአቢሲኒያ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ ብቻ የ32 አስጎብኚ ድርጅቶችን ሒሳብና ንብረት ያገደ ሲሆን፣ ድርጅቶቹ እንደ ደረጃቸው ግብር በሚከፍሉባቸው ቅርንጫፎች በኩል ሒሳቦቻቸውን ለሚያንቀሳቅሱባቸው ባንኮች ተመሳሳይ የዕግድ ደብዳቤ መጻፉን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ድርጅቶቹ የንግድ ፈቃድ ማሳደስ እንዳልቻሉና የተወሰኑት ሰነድ ከቢሮ አውጥተው እየዘጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በሦስት የተለያዩ ባንኮች ያለን አካውንት ታግዷል፡፡ ገንዘብ ማስገባት እንችላለን ግን ማውጣት ወይም ማንቀሳቀስ አንችልም፡፡ ባንኮቹ በገቢዎች ሚኒስቴር ደብዳቤ መሠረት አካውንቶቻችንን እንዳገዱ ነግረውናል፤›› ሲሉ ስሙ እንዳይገለጽ የተፈለገ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
‹‹እስከ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ብናስገባም ምላሽ አላገኘንም፡፡ የአስጎብኚ ድርድቶቹ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ የቱሪዝም ሥራ እጅግ በመጎዳቱ እንኳን ግብር ልንከፍል ከመንግሥት ዕርዳታ ስንጠብቅ ነበር፤›› ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በአገሪቱ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የመዳረሻ ቪዛ (Arrival Visa) መስጠት መንግሥት በመከልከሉ፣ ቱሪስቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መምጣት አለመቻላቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአስጎብኚ ድርጅቶች ባለቤቶች ገልጸዋል፡፡
‹‹የተወሰኑ አባላቶቻችን አካውንት ተዘግቷል፡፡ ችግሩ በሰላም ይፈታል ብለን ስንጠብቅ ስለነበር ስንሰማ ደንግጠናል፡፡ ድርጅቶቹ እንክፈል ቢሉ እንኳን አይችሉም፡፡ ምክንያቱም የባንክ አካውንታቸው ዝግ ነው፡፡ ከአካውንት ወደ አካውንት ካልሆነ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ተከልክሏል፤›› ሲሉ የታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ናሆም በቀለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ በዚህ ማኅበር ሥር 40 አስጎብኚዎችና በኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር ሥር ደግሞ 200 አባላት አሉ ይላሉ፡፡ በሁለቱም ውስጥ አባል ሳይሆኑ የሚሠሩም መኖራቸውንና ቁጥራቸው መቀነሱን፣ አብዛኞቹ አስጎብኚዎች የተጋነነ ግብር እንደተጣለባቸውና እስከ 400 ሚሊዮን ብር ክፈሉ የተባሉ እንዳሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
‹‹ወደ ገጠር ባሉ የቱሪስት መዳረሻዎች ደረሰኝ ስለሌለ አብዛኞቹ ደረሰኝ የሌላቸው ወጪዎች›› በሚል ይመዘገባሉ፡፡ ገቢዎች ግን ስለማይቀበል እንደ ገቢ ቆጥሮ ታክስ ክፈሉ ይላል፤›› ይላሉ አቶ ናሆም፡፡ አንዳንዶቹ የአስጎብኚ ድርጅቶች ባለቤቶች ያደረጓቸው ግብይቶች ድርጅቶቹ እንዳደረጉ ተደርጎ እንደተቆጠሩም ገልጸዋል፡፡ አስጎብኚ ድርጅቶች ቫትና 35 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/index ... icle/23788