Page 1 of 1

በኮሮና ወረርሽኝና በፀጥታ ችግሮች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የቱሪዝም ገቢ መታጣቱ ተገለጸ (Reporter)

Posted: 19 Nov 2021, 23:20
by sarcasm
በኮሮና ወረርሽኝና በፀጥታ ችግሮች ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የቱሪዝም ገቢ መታጣቱ ተገለጸ (Reporter)

የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ በኮሮና ወረርሽኝና በፀጥታ ችግሮች ሳቢያ ክፉኛ በመጎዳቱ፣ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መታጣቱ ተነገረ፡፡ የቱሪዝም አስጎብኚ ባለሙያዎች ማኅበር አባላቱ ገቢያቸው መድረቁን ተናግረዋል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስቴር በበኩሉ የዘርፉ ገቢ እንዲሻሻል የቱሪስት ምንጭ የሆኑ አማራጭ የገበያ ዕድሎችን በማፈላለግ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

‹‹እኛ በቅጥር ወይም በኮንትራት ሳይሆን ከምንሰጠው አገልግሎት በምናገኘው ክፍያ ነው እንጀራችን የተመሠረተው፡፡ አገልግሎቱን የሚፈልግ ቱሪስት ጠፋ ማለት የእኛም ገቢ ተቋረጠ ማለት ነው፤›› ሲሉ የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አሸናፊ ካሳ ይናገራሉ፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘው የቱሪዝም ዘርፍ ባለፈው አንድ ዓመት አገሪቱ ባጋጠማት የፀጥታ መደፍረስ መሆኑን፣ የአስጎብኚ ባለሙያዎች ገቢም በአብዛኛው መድረቁን አቶ አሸናፊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የዘርፉን መጎዳት ያረጋገጡት የቱሪዝም ሚኒስቴር የመዳረሻ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ በበኩላቸው፣ ‹‹በኮሮና ወረርሽኝና በፀጥታ ችግሮች ኢትዮጵያ ከዘርፉ ሁለት ሦስተኛ ወይም ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አጥታለች፤›› ሲሉ የዘርፉን ጉዳት ገልጸዋል፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/index ... icle/23786