በታላቁ ምኒልክ ወምበር ላይ የተቀመጠው አቢይ አህመድ አንገቴ ይቀላል እንጂ በኢትዮጵያ ያሜሪካ ተላላኪ መንግስት አይፈጠርም ብሎ የኢትዮጵያን ምስለ ባህሪና ስነ ስብዕና ካስረገጠበት ታሪክ አንስቶ የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያዊ የአሜሪካን ፖለቲካ ሚዛን እስከ ደፉብት አስገራሚ ድል፣ በትግሬ ባንዳ ከተኛበት ተጨፍጭፎ ዞሮ ትህነግ የሚባል የትግሬ ድርጅት ከኢትዮጵያ ምድር የደመሰሰበት ታሪክ፣ የአሜሪካን መፈንቅለ መንግስትና ወረራ፣ ያለም ድርጅትና ሚዲያ ኢትዮጵያን ለማንበርከክ የካቡት የቅኝ ገዥ አሸዋ ግምብ የደረመሱበት ታሪክ፣ ኢትዮጵያ ፈረሰች ተረት ተረት ምድርና ሰማይ ባናወጠ የአንድ ሕዝብ፣ የአንድ አገር፣ የአንድ መንግስት አንድነት አለምን ያስደመሙበት ይህ የዘመናች ዳግም አድዋ ገና፣ ገና መጻፍ መጀመሩ ነው!
ኢትዮጵያን ወዳጅ ማድረግ ይቻላል፣ ግን ኢትዮጵያን መድፈር ፍጹም አይቻልም። ደሞ አሁን በነካ እጃችን በያዝነው ህብረትና መንፈስ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከልመናና እርዳታ ነጻ አውጥተን አሜሪካ ለኢትዮጵያ እንደ ማታስፈልግ ላንዴም ለሁሌም ማረጋገጥ አለብን! ያሜሪካ ስንዴና ተራድኦ ከኢትዮጵያ ምድር መወገድ አለበት!
ሰርተን በመብላት ነጻ ሕዝብ እንሁን ! ጥረን በመክበር ታላቅ ሕዝብ እንሁን! አንድ በመሆን ሃያል አገር እንሁን !! ኬር !!!