"የኣብይ ኣህመድ መንግስትና ደመቀ መኮንን የሚመራው ተስፋፊ ልሂቅ ጦርነቱ በነሱ ተሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ በትክክል ኣውቀውታል" ጌታቸው ረዳ
Posted: 18 Nov 2021, 09:23
የኣብይ ኣህመድ መንግስትና ደመቀ መኮንን የሚመራው ተስፋፊ ልሂቅ በትግራይ ህዝብ ላይ የጀመሩት የዘር ማጥፋት ጦርነት በወታደራዊ መስኩ በነሱ ተሸናፊነት እንደሚጠናቀቅ ኣብይም ደመቀም በትክክል ኣውቀውታል:: ይሁን እንጅ ኣዲስ ኣበባ ውስጥም 'ቀኝ ግራ' የሚል ስልጠና ሰጥተውና ኣስፋልት ዳር ምሽግ ሰርተው ተጨማሪ ደም መፋሰስ ለመፍጠር የሚቻላቸውን እያደረጉ ይገኛሉ:: በፍፁም ኣይሆንላቸውም ከነፉከራቸው መቀመቅ ይወርዷታል:: የኛ ሰራዊት መንዝና ግሼ ከገባ በሁዋላ ጭምር የወሎ ግንባር እያሉ ደጋፊዎቻቸውን የሚያጨብረብሩት የኣብይ ተላላኪዎች ሽንፈታቸውን ላለመቀበል የሚያነሷቸው ሦስት ኣስቂኝ ምክንያቶች ኣሉ::
ኣንደኛ: ሰራዊቱ በኣሻጥር ምክንያት ያለውግያ በመፈርጠጡ ቦታ ለቀቅን እንጅ በውግያ ኣልተሸነፍንም ይላሉ:: እስካሁን ያለቀው በኣስር ሽዎች የሚቆጠር ወታደር: ልዩ ሃይል: ሚሊሻና ፋኖ ተራ ኣሃዝ ነው:: ታንኩና መድፉን እርሱት:: ለነገሩ ኣሻጥርን ያስቻለን እውነታ የፈጠረ ፖለቲካ ካለ ደግሞ የራሳቸው ራስ ምታት ነው::
ሁለተኛ: ወያኔ/ጁንታው መዘዞየደረሰው በውግያ ሳይሆን በፕሮፓጋንዳ ነው የሚል ተረት ነው:: ይህንን ለመቋቋም ደግሞ በቁጥጥራችን ስር የገቡ ከባቢዎችን ህዝብ ወሬ የፈታው ባንዳ እያሉ ማብጠልጠል ይዘዋል:: ሰራዊታችን የደረሰበት ቦታ ላይ የደረሰውና ኣሁንም በፍጥነት በመገስገስ ላይ የሚገኘው ከፀረ ህዝብ ሰራዊት ጋር ገጥሞ በሚገባ ኣሸንፎ ነው:: ግብኣተ መሬታቸውን የምናረጋግጠውም የቀረውን ሃይላቸውን ደምስሰን ነው:: እስካሁን በተደረገው ውግያ የተሸነፈው የኣማራን ህዝብ ጭምር ለሞትና እንግልት የዳረገውን ፀረህዝብ ሰራዊት እንጂ ያማራ ህዝብ ኣይደለም::
ሦስተኛ: ኣሁን እየተደረገያለው ጦርነት በምዕራባውያን ጣልቃገብነት የሚደገፍና ኣፍሪካውያንን ኣንገት ለማስደፋት የታሰበ ዘመቻ ነው የሚል ነው:: በነገራችን ላይ ኣብይ ኣህመድ የምዕራባውያን ዋና ተላላኪ ሆኖ ኖቤል መሸለሙን ረስቷል:: ኣብይ ኣህመድ ኢሳያስ ጋር 'የሰላም ስምምነት' ጀዳ ውስጥ ሲፈራረም የወቅቱ የኣፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የነበሩት ፖል ካጋሜ በስነስርዓቱ ላይ እንዲገኙ የሳውዲ ኣረብያ መንግስት ያደረገላቸውን ጥሪ እንዲሰረዝ ያደረገ መሆኑን ኣብዛኛው ኣፍሪካ ኣይዘነጋም:: ኣሁን ደርሶ ኣፍሪካ ወይም ሞት ከውድቀት ኣያድንም:: ለማንኛም ልጆች ሆነን ያልታሰበ ሽንፈት የገጠመው የሰፈር ጉልቤ የቀጠቀጠውን ኮስማና ልጅ ድል ላለመቀበል ሌላ ሃገር ያለን ጉልቤ ተጠያቂ እንደሚያደርገው ዓይነት ነው:: ለማንኛውም ኣብይ ለውድቀቱ Uncle Samን ተጠያቂ ስላረገ የትግራይና የኦሮሞን ሰራዊት ድል ኣያሳንስም::
በነገራችን ላይ ከእውነት ጋር ሳይታረቁ መቃብር ለሚወርዱት ሽፍቶች ፃድቃኔ ማርያም ትሁናቸው ከማለት ውጭ ምንም ማለት ኣይቻልም::
ትግራይ ትስዕር!

Please wait, video is loading...