20m ·
አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር ተወያዩ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ ጄፈሪ ፊልትማን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው ከአሸባሪው ሕወሐት ጋር የሚደረገው ጦርነት ስለሚቆምበት መንገድ የአሜሪካ ሐሳብ ምን እንደሆነ በልዩ ልኡኩ በኩል የተነሣ ሲሆን፣ አቶ ደመቀም የኢትዮጵያን አቋም ማስረዳታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ አስታውቋል።
