Page 1 of 1

ለታላቋ ኣዳነች ኣበቤ - [ሰሞንኛው ኤርትራዊ ግጥም]

Posted: 17 Nov 2021, 03:51
by Meleket
ተስቦ” የት ደረሰ? “ጽዳት” ዘመቻዉስ እንዴት ነው?

ለታላቋ ኣዳነች ኣበቤ

ነግሬሽ ነበረ ባጥር ተንጠልጥዬ፣
ፈንግሉ” ይገልሻል “ጽዳት” ከዘገዬ!

ይህን የነገርኩሽ በኣምቦ ኣስመስዬ፣
እንድትወስኝ ነበር፡ ትሰሚያለሽ ብዬ።
:mrgreen:
Meleket wrote:
04 Mar 2018, 03:03
“አምቦ፣
አንቺ የደም ገንቦ”፣
ከወዲያኛው መንደር የመጣው ተስቦ
ፍልቅልቅ ቀየሽን በጭካኔ ከቦ፣
ስንት ንጹሓንን ማገደ ጠራርቦ።

ለሰሚ ሚገርመው በጣም የሚያስደስተው፣
ያ ሁሉ ወገንሽ እጁን ያጣመረው፣
ያ ሁሉ ወገንሽ ደምሽ ያቆራኘው፣
ነግ በኔ በማለት ችግርሽን ሊጋራው፣
ያን ክፉ ተስቦ ድራሹን ሊያጠፋው፣
እነሆ ጀምሯል ትግሉ ተፏፉሟል፣
ማን ምን እንደሆነ ሜዳው ላይ ይታያል።

ሚሊዮኑ ወገንሽ ነግ በኔ ካላለ፣
ፈውስ መፈለግ ላይ አንቺን ካልመሰለ፣
በጽዳት ዘመቻ ካንቺ ጋር ካልዋለ፣
ተስቦው ቀስ በቀስ ሁሉን ያጋድመዋል እየፈነገለ።

ስለዚ ወገኔ እየተስተዋለ፣
ለመብትህ መቆም ነው አሁን ግዜ ሳለ።