የትግራይ ህዝብና መንግስት ለአማራ ህዝብ፣ ለአማራ መንግስት ሰራተኞችና ለአማራ ታጣቂ ሃይሎች ራሳችሁን ከነዚህ የጥፋት ቡድን እኩይ ተግባር እንድትታደጉ ያስተላለፈዉ ጥሪ:-
Posted: 16 Nov 2021, 11:33
ከትግራይ መንግስት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የትግራይ ህዝብና መንግስት ለአማራ ህዝብ፣ ለአማራ መንግስት ሰራተኞችና ለአማራ ታጣቂ ሃይሎች ራሳችሁን ከነዚህ የጥፋት ቡድን እኩይ ተግባር እንድትታደጉ ያስተላለፈዉ ጥሪ:-
የተከበራችሁ የአማራ ህዝቦች!
ፋሽስቶችና ወራሪዎች ለስልጣናቸው ሲሉ የሚያውጁት የክተት ጥሪ በመቃወም ራሳችሁን ከአደጋ እንድትታደጉ የትግራይ መንግስት ታላቅ ጥሪ ያስተላልፋል። በተግባርም ሲታይ የትግራይ ህዝብና የአማራ ህዝብ እርስ በራስ ጠላቾች ሳይሆኑ የሚደጋገፉ ህዝቦች እንደሆኑ የሚያመላክቱ በአሁኑ ግዜ የትግራይ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው የአማራ ክልል ታላላቅ ከተሞችና ገጠር ወረዳዎች የህዝቡ አቀባበልና ሰራዊታችንም ለህዝቡና ለምርኮኞች ያለዉ አያያዝ ህያዉ ምስክር ነዉ።
በአማራ ክልል የምትገኙ የከተማ፣ የወረዳና የቀበሌ መንግስታዊ መዋቅሮች የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ የትግራይ መንግስትና ሰራዊት በአማራ ክልል የሚገኙ ህዝቦች የሚገለገሉባቸዉ መስተዳድሮች የማፍረስ ፍላጎትም ምኞትም እንደሌለዉ ከዚህ ቀደም ገልፀዋል።
አሁንም ቢሆን በዚህ የሚቀይረዉ አቋም እንደሌለዉ ተገንዝባቹሁ የትግራይ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎችም ይሁኑ በሌሎች አከባቢዎች ህዝቡ የሚፈልጋቸው አገልግሎቶች መሰጠት እንድትቀጥሉና ህዝቡ የአገልግሎት መስተጓጎል እንዳይገጥመዉ ሃላፊነታችሁ እንድትወጡ የትግራይ መንግስት ያሳስባል።
በአማራ ክልል የምትገኙ ታጣቂዎች እንደሚታወቀዉ የትግራይ ሰራዊት የአማራ ክልል አካባቢዎች መቆጣጠር ከጀመረበት ከሐምሌ ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ በየአካባቢው ያላቹህ ታጣቂዎች ወደ ትግራይ ሰራዊት እስካልተኮሳቹህ ድረስ ትጥቃችሁ ይዛችሁ አካባብያቹህ እንድትጠብቁ የትግራይ መንግስት ያስተላለፈዉ መልእክት በውል በመረዳት ሕይወታችሁን በከንቱ ከመጥፋት ሰለታደጋችሁ ልትኮሩ ይገባል።
አሁንም ቢሆን የትግራይ ሰራዊት ይህ ሰዉ በላ ስርዓት ለመቅበር ግስጋሴዉ እየቀጠለ ባለበት ወቅትና ግዜ በየአካባቢው የምትገኙ የአማራ ክልል ታጣቂዎች በሰላም ከነትጥቃቹህ መኖር እንደምትቹሉ ተገንዝባቹህ በሌለ ትርክትና የዉሸት ፕሮፖጋንዳ ተደናግራችሁ ወደ አላስፈላጊ ሞትና ደም መፋሰስ እንዳትገቡና ከወንጀለኞቹ እኩይ ተግባር እንድትቆጠቡ የትግራይ መንግስት በጥብቅ ያሳስባል።
በመጨረሻም መላዉ የአማራ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ይህችን አገር ለብተና እና ለእልቂት ለዳረግዋት ፋሽስቶችና ወራሪዎች ስልጣን ሲባል የአማራ ህዝብ ሕይወትና ደም በከንቱ መጥፋትና መፍስስ እንዲቆም ድምፃችሁን እንድታሰሙና ስርዓቱን ለማፍረስ ድርሻችሁን ልትወጡ ይገባል፡፡
የትግራይ መንግስት
ህዳር 7/2014 ዓ.ም
መቐለ

Please wait, video is loading...