Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Ejersa
Member
Posts: 3978
Joined: 05 Nov 2019, 10:39

የሳምሪ አባል የሆኑና በማይካድራው የግፍ ወንጀል ላይ የተሳተፉ ሶስት ግለሰቦች በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ!

Post by Ejersa » 15 Nov 2021, 14:48

ግለሰቦቹ በሱዳን አድርገው ወደየመን ከሄዱ በኃላ ከየመን በስደተኛ ስም መግባታቸው ተገልጿል።

ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ተልእኮአቸውን በሚስጢር ለማከናወን ሲንቀሳቀስ በህዝብ ጥቆማ ትብብር መያዛቸውን የኢሳት የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ በዛሬው ዕለት በስሚት የኮንዶሚኒየም ግንባታ ሳይት በጥበቃ ድርጅት ውስጥ ተደብቀው መያዛቸውም ታውቋል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች የሳውዲ ፖስፖርት ያላቸው እንዲሁም የአዲስ እበባ የነዋሪነት መታወቂያ የሀሰት በማሰራት ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ የአሽባሪውን ህወሀት ተልዕኮ ሊፈፅሙ ሲንቀሳቀሱ በህብረተሰቡና በዙሪያው ባሉ ሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ውለዋል።