ዘንድሮ እነርሱ ናቸው ከአድዋ የሚመጡት የሚል አይጠፋም
Fitsum Hagose
ከጊዮርጊስ እስከ አድዋ ድልድይ
Bin Seid
አድዋ የለ አጎዋ የለ አርፈህ መቀመጥ ነው።
Ted Zed
አድዋ ድልድይ ድረስ ነው...እዛም ቢሆን ከመሸ የመድረስ ግዴታ የለባቸውም አዲስ አበቤ አምሯል አዋጁን ተንተርሶ በጊዜ ነው ሚተኛው
Daniel Abraham
ከተክለሃይማኖት እስከ 22::
https://www.facebook.com/abel.asrat.5/p ... 1124970530
Abiy Ahmed ignored the below plea and advice, and we all can see where his adamant behavior has taken him.
"አዲስ የሰላም መንገድ መታሰብ አለበት!"
(ያሬድ ሹመቴ) ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ
የጉዞ ዓድዋ 8 ፍፃሜ ዝርዝሩን በተመለከተ እዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ስለምታገኙት ሙሉውን አጋርቻችኋለሁ። መልካም ንባብ፤
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
* የዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ ተጓዦች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሶሎዳ ተራራ አናት ድረስ መዝለቅ አልቻሉም። ምን ገጠማችሁ?
በዘንድሮው ጉዞ ዓድዋ በእኛ እምነት፣ በበቂ ሁኔታ በስኬት ተልዕኳችንን አጠናቀናል ብለን ነው የምናምነው፡፡ እርግጥ ነው ዓድዋ አልገባንም። ዓድዋ ያልገባንበት ምክንያትም ግልፅ ነው። አሁን በትግራይ ላይ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ከአላማጣ በላይ ጉዟችንን መቀጠል አልቻልንም። እኛ ሁሌም ማረጋገጥ የምንፈልገው ጉዞ ዓድዋ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መካሄዱን ለአገር የምናረጋግጥበት መንገድ ነው።
በመሳሪያ ታጅበን መጓዙን በፍፁም አልፈለግነውም። እኛ በተለየ መንገድ በመሳሪያ ታጅበን ብቻችንን ሆነን ብናልፍ፣ ሰላም ያጣ ህዝብ በአካባቢው እያለ እኛ ሰላም እንዳለ አድርገን ተጉዘን ብንጨርስ፣ ይሄ ለሌላው የተሳሳተ መልዕክት ማስተላለፍ ስለሆነ ተገቢ አይደለም። በዚህ ምክንያት ሰላም እስካለበት ቦታ ድረስ ያለውን ተጉዘን እዛ ላይ መግታቱ በቂ ነው በሚል ፍጻሜያችንን አላማጣ ላይ አድርገናል።
* በፀጥታ አካላት እንዳታልፉ ተደርጋችሁ ነው ወይስ ራሳችሁ ናችሁ ጉዞውን ያቆማችሁት?
ከፀጥታ አካላት ጋር ምክክር ነው ያደረግነው እንጂ የከለከለን የለም። እንዳልኩሽ ከአላማጣ በኋላ የሚኖረው ጉዞ አስቸጋሪ እንደሚሆን ነው በፀጥታ አካላት የተገለጸልን። አንዱ የነበረው አማራጭ በፀጥታ ሀይል ታጅቦ መሄድ ነው። ይህም ቢሆን አስቸጋሪ ነው የሚሆነው። እኛም ጉዞ ዓድዋ የሰላም ጉዞ መሆኑን የምናረጋግጥበት መንገድ በመሆኑ ታጅበን የመጓዙን ነገር በጭራሽ አልፈለግነውም።
የፀጥታ ችግሩ የተከሰተው ጣሊያን አገራችን (ዓድዋ) ገብቶ ቢሆን ኖሮ፤ አስፈላጊወን መስዋዕትነት ከፍለን ጉዞውን እንቀጥል ነበር። አሁን አገራችን ላይ የተከሰተው ጉዳይ አንደኛው ወገን “የህግ ማስከበር” ይለዋል፤ ሌላው ወገን “ጦርነት” ይለዋል። ግራና ቀኝ መሳሳብ ስላለ ቃላት አጠቃቀም ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በእኛ እምነት ወቅታዊው የአገራችን የፀጥታ ሁኔታ አስጊ ነው ብለን ነው የምንጠቅሰው።
* ጉዞው ሲጀመር የወቅቱ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ለጉዞው አያሰጋችሁም ወይ የሚል ጥያቄ አቅርቤልህ “ጉዞ ዓድዋ “አገር ሰላም ስትሆን የምንተገብረው አገር ሰላም ሲደፈርስ የምንሰርዘው ጉዞ አይደለም የህዝቡን ሁኔታና ችግር ቦታው ላይ ተገኝተን እንጋራለን” የሚል ምላሽ ሰጥተኽኝ ነበር?
ትክክል ነው። ቅድም እንዳልኩሽ ጉዞውን በተመለከተ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ምክክር አድርገን ነበር። ክልከላ አልነበረም። ምን ማለት ነው? የፀጥታ ሀይሉ ከዚህ አልፋችሁ እንድትጓዙ አንመክርም ነው ያሉት። ይህ በሆነበት ሁኔታ ሃላፊነቱን ወስደን ብንጓዝና ከተጓዦች መካከል ህይወቱን የሚያጣ ቢኖር፣ ለሀገር ሌላ ችግር መፍጠር ነው የሚለውን ነገር ነው ያየነው። አየሽ አንድ ነገር በተጓዦች ላይ ቢከሰት፣ በአገር ላይ ሌላ የመፋጫ፣ የመዋቀሻና ጎራ ለይቶ መደባደቢያ አጀንዳ ነው የምንሆነው።
በነገርሽ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገው መንግስትም ሆነ የቀደመው የትግራይ ክልል ሀይል ከእኛ ጋር የተለየ ጠብ የለውም። ከዚህ ቀደም ትግራይን ከምንረግጥበት ዕለት አንስቶ እስከ ፍፃሜው ሶሎዳ ተራራ ድረስ የእነሱ ኃይል አጅቦ፣ እያበላ እያጠጣና እያስተናገደ ይወስደን ነበር- ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ማለቴ ነው። ምናልባት ቅሬታ ያለን የመጨረሻዋ የመድረክ ቀን ላይ እንደ ልባችን የዳግማዊ አፄ ምኒልክንና የሌሎችን ጀግኖች ስም እየጠራን ለመዘከር ገደብ የተጣለብን መሆኑን ነው። በተረፈ በደህንነት ደረጃ እኛን ችግር ውስጥ የሚያስገባ ነገር በፊት አልነበረም። ያኔ የሚጠብቁንና አጅበው የሚወስዱን አካላት እኛን ያጠቁናል ብለን አናስብም። ነገር ግን አሁን ያለው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ግልፅ ነው። ይህንን እያወቅን “ከዚህ ማለፋችሁ አይመከርም” እየተባልን፣ ሃላፊነት ወስደን መሄድ ለአገር የሚያመጣውን ችግር በማየት ለማቆም ተገድደናል።
* እንደሰማሁት ከጉዞው አስተባባሪዎች መካከል ጥቂቶቻችሁ ከመቀሌም አልፋችሁ ሁኔታዎችን ለማየትና ህዝቡን ለማነጋገር ሞክራችኋል”፡፡ እስኪ ያያችሁትን የታዘባችሁትን ጉዳይ አጋራን?
እውነት ነው፤ አስተባባሪዎቹ ከአላማጣ ተነስተን መቀሌን አልፈን እስከ ውቅሮና አካባቢው ያለውን ሁኔታ ለመገንዘብ ሞክረናል። ያየነው ችግር በእኛ እምነት፣ በኢትዮጵያ ለዘመናትና ለትውልድ የሚተርፍ ቁርሾ እንዳያፈራ የሚያሰጋ፣ የስነ-ልቦና ጉዳት መድረሱን አስተውለናል። እናም የትግራይ ህዝብ አሁን ባለበትና በተያዘው መንገድ የሚተውና በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ፣ ሁኔታው እስከ ዛሬ በተያዘው የብሽሽቅ መንገድ ከቀጠለ… ምናልባትም ምን ሆናል መሰለሽ? ዶጋሊ የኤርትራ ክፍል በመሆኗ የዶጋሊ ድልን ማክበር እንዳቆምነውና ራስ አሉላንም አብረን መዘከር እንዳቆምነው ሁሉ ዓድዋንም ላንዘክር የምንችልበት ጊዜ ይመጣል።
እንደሚታወቀው በአብዮቱ ዘመን የዶጋሊ ድል በየዓመቱ ጥር 18 ላይ ለዶጋሊ መታሰቢያ ይደረግለት ነበር። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትነጠል ይሄንንም ድል ማክበር አቆምን። ራስ አሉላም አይዘከሩም። አሁን ባለው ሁኔታ እኛ ዓድዋ አልገባንም ማለት፣ በቀጣይ ዓድዋን ለማክበር ራሱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንደ አገር መግባታችንን ያሳያል። ምክንያቱም እኛ ከህዝቡ ጋር ለተጨማሪ ብሽሽቅ መግባት አንፈልግም። ለምን ካልሽኝ ህዝቡ ጥያቄ አለው።
እያንዳንዱ ቦታ ላይ ያስተዋልነውና ያየነው ነገር በሁለት መንገድ የተወጠረ ነው። ከውጪ ያለውና የትግራይን ጉዳይ አንስቶ የሚሟገተው አካል የያዘበት መንገድና መንግስት ጉዳዩን የያዘበት መንገድ ከፍተኛ ውጥረት ያለበት ነው። መሀል ላይ ያለውን ህዝብ ስታይው ግን ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጉዳት ላይ መውደቁን ትረጂያለሽ።
የወደሙ ንብረቶች አሉ፣
መቀሌን ስንመለከት የከፋ የሚባል ቁሳዊ ጉዳት የለም። የሞራልና የኢኮኖሚ ውድመት ግን አለ። እንቅስቃሴው በሙሉ ዝግ ነው። ስለዚህ ኢኮኖሚው እየሞተ ሰው እንዴት በልቶ ሊያድር ይችላል? እንዴትስ ሰርቶ መግባት ይችላል? ይህ ትልቅ ችግር ነው።
ውቅሮን ስንመለከት ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት፣ የተዘረፉ ቤቶች፣ የተሰባበሩ እቃዎች ፣ በጥይት የተበሳሱ መስታዎቶች፣ የተዘረፉና ኦና ኦና የቀሩ ቤቶችን አይተናል። በየመንገዱ ግራና ቀኝ ላይ በርካታ የወደሙና የተቃጠሉ የጦር ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ተመልከተናል። መንገዶችም አሁን ታድሰው ይሆናል እንጂ ያ ሁሉ ውድመት ሲደርስ አብረው ወድመው እንደሚሆን መገመት አያዳግተም። የመታደስ ምልክትም አይተናል።
በሌላ በኩል፤ ህዝቡን ለማናገር ሞክረን ነበር። እኛንም ይቀበሉን የነበሩ ሰዎች ጋር ለመነጋገር እንደሞከርነው ኢትዮጵያዊነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት እንደፈጠረባቸውና የስነ-ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው አስተውለናል። በምን ምክንያት ይህ ጉዳት ደረሰባቸው ብትይኝ እኔ ልተነትነው አልችልም። መልሱ ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል። ግን በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ሰላም አግኝቷል ብሎ ተረጋግቶ መቀመጥ እንደ ሀገር ዋጋ ያስከፍለናል።
የዓድዋን ድልም እንዳናከብረው የሚያደርግ የትውልድ በደል ወይም ጥላ ሊያጠላበት ይችላል የሚለው ስጋትም አለን።
*ተጓዦች ጉዞውን መጨረስ እንደማይችሉ ሲነገራቸው ምን ተሰማቸው?
በፀጥታ አካላት ጉዞውን መጨረስ እንደማንችል ሲገለጽልን ተጓዦች ቁጭት ነበር የተሰማቸው። ቁጭቱ ዓድዋ አለመግባታችን ሳይሆን እንዳንገባ ያደረገን ምክንያት ነው። የመጀመሪያ ፍላጎታችን የነበረው ዓድዋ መግባት ነው። ዓድዋ መግባት እንፈልጋለን። እንደ ምንም ብላችሁ ዓድዋ አድርሱን አላልንም። እንደዛ ካልናቸው አጅበው ነው የሚወስዱን። ይህንን ካደረግን ቅድም እንዳልኩሽ “እኛ ሰላም ደርሰን ተመልሰናል፤ ሁሉም ሰላም ነው” የሚል የተሳሳተ መልዕክት ከማስተላለፍ ውጪ ለአገራችንም የምናተርፈው ለህዝቡም የምንፈይደው ነገር የለም። እኛም አጅባችሁ ውሰዱን አላልንም እነሱም አልጠየቁንም።
ቀደም ሲል እንደገለፅኩልሽ ጉዟችን ስኬታማ ነው የምንለው እስከምንችለው ተጉዘንና ያየነውን አይተን ተመልሰናል። ይህንን ለህዝብ መናገርና ማሳወቅ ደግሞ ሌላ ስኬት ነው የምንለው። ስለዚህ ትግራይ ላይ ያለው ጉዳይ እስካሁን በተያዘው ሁኔታና መንገድ ተይዞ የሚቀጥል ከሆነ ምናልባትም የዓድዋ ድልን ልናጣም እንችላለን። ይሄንን በአፅንኦት መናገር እፈልጋለሁ።
*በትግራይ ያለውን ጉዳይ በምን መልኩ መፍታት ይቻላል ትላለህ? ምን ምን አማራጮችስ ይታዩሃል?
እንግዲህ ከስር መሰረቱ መፈተሽ ያስፈልጋል። አሁን በተካሄደው የፀጥታ ውትርክ በመንግስት አካባቢ ውትርኩን ከዓድዋ ጦርነት ጋር የማመሳሰል አዝማሚያ ታይቷል።
ዓድዋ ከውጭ ወራሪ ጋ የተካሄደ የነጮችን የበላይነት መንፈስ ሰብሮ የሰው ልጆችን እኩልነት ያረጋገጠ ለዓለም የነፃነት ነፀብራቅ የታየበት ድል ነው።
አሁን ያለው የአገራችን ወቅታዊ ውትርክ በታሪክ ዓይን ስናየው ሰገሌን እንጂ ፈፅሞ ዓድዋን አይመስልም። ታሪክ እንደሚነግረን፤ ሰገሌ በንጉስ ሚካኤልና በራስ ተፈሪ የመሀል አገሩ ጦር መሐል የተደረገ ጦርነት ነበር። በወቅቱ በስሙ ቤተ-ክርስቲያን እስከ መሰየም ድረስ ተደርሷል። ዘመን ካለፈ በኋላ ግን 100ኛ ዓመቱ ሲደርስ እንኳን ሊከበር ሳየታሰብ ነው ያለፍው።
ስለዚህ የወቅቱ ውትርክ የዓድዋን ሳይሆን የሰገሌን ነው የሚመስለው። የትግራይን ጉዳይ በአዳዲስ መንገዶችና የመፍትሄ ሀሳቦች፣ እስከዛሬ ባልተካሄደበት አዲስ መንገድ ሰላም መፈጠር አለበት። ይሄንን ከእኛ ውጪ ያሉ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችም ሆኑ ማህበራዊ አንቂዎች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። በምንም ተባለ በምንም. ህዝቡ ከደረሰበት የህይወት ጫና፣ የስነ-ልቦና ስብራትና ምስቅልቅል መውጣት አለበት። ለዚህ ደግሞ አዲስ የሰላም መንገድ መታሰብ አለበት ባይ ነኝ።
* የዘንድሮው የዓድዋ ተጓዦች፣ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ቀሪውን መንገድ ለመጓዝና ሶሎዳ ተራራ ለመውጣት ያሰቡት ይኖር ይሆን?
ሁሉም በቀጣዩ ዓመት ሰላም ከሆነ ከቆሙበት ከአላማጣ ጀምረው ቀሪውን ለመጓዝ አቅደዋል የሚወሰነው ቀጣዩ የሀገራችን ሁኔታ ነው። እንዳልኩሽ በፀጥታ ኃይሉ ከአላማጣ በኋላ መጓዝ አስቸጋሪ እንደሆነ ሲሰሙ የቆጫቸው ጉዞውን እንዳያጠናቅቁ ያደረገው ምክንያት ነው። እኛ አላማጣ ላይ ተጓዦቹን አቁመን እስከ ውቅሮ ስንጓጓዝ ከአላማጣ እስከ ውቅሮ ባለው 200 ኪ.ሜ ውስጥ በአካባቢው ጦርነቱ የጣለውን አስከፊ ጠባሳ አይተናል። ንብረት ወድሟል፣ ሰው ከቤት ከንብረቱ ተፈናቅሏል፣ ወጣቶች በአካባቢው አያታዩም፣ እንቅስቃሴው እንደ ድሮው አይደለም። በዚህ መሃል ሰው መሞቱ አይቀሬ ነው። ይህ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ ህዝቡ በስነ-ልቦና የሚያገግምበትና የሚታደስበት አዲስ የሰላም መንገድ መፈጠር አለበት።
ይህ ካልሆነ የዓድዋ ድልን ማክበር ቅንጦት ሊሆን ነው ማለት ነው። በነገርሽ ላይ በቀጣዩም ዓመት እንጓዛለን ስንጓዝ 600 ላይ ነው የምንቆመው 700 ላይ ነው? አናውቅም ። እኛ ግን እንጓዛለን።
ጉዞውን አትቀጥሉም ሲባልና አድዋ መድረስ እንደማንችል ስናረጋግጥ አምባላጌ ብናከብር ብለን ጠይቀን ነበር። አምባጌ አንዱ ጦርነቱ የተካሄደበትና ቀረብ ያለ ስለሆነ። እዛም ማክበር እንደማንችል ከፀጥታ አካላት ሲነገረን ሀዘን ብቻ ሳይሆን ለቅሶም ነበር። ሁሉም ነው የተላቀሰው። ለቅሶው ለምን ዓድዋ አልገባንም አይደለም የቀረንበት ምክንያት ነው ደጋግሜ እንደነገርኩሽ በተለይ አንዲት ተጓዥ እምባ እያፈሰሰች
“ዓድዋ አለመግባቴ አይደለም ዓድዋ ያልገባሁበት ምክንያት ነው የሚያስለቅሰኝ ለልጆቼ የማስተላልፋት አገር እንደዚህ መሆኗ ያስለቅሰኛል” ነው ያለችው እና የሚያሳዝን ነገር ነው።
ዞሮ ዞሮ በቀጣይ ከአላማጣ ተነስተው ይጓዛሉ አገር ሰላም ከሆነ። በቀጣይ ዓመት ዓድዋን ማክበር ከፈለግን ከላይ የጠቀስኳቸው ብዙ የቤት ስራዎች በወቅቱ መሰራት አለባቸው እላለሁ አመሰግናለሁ።
https://www.facebook.com/shumeteyared/p ... 2590013874