የጥቅምት ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር የ40.7% ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቆመ - Reporter
Posted: 15 Nov 2021, 10:23
በወርኃ ጥቅምት 2014 ዓ.ም. የነበረው የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር የ40.7 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት አስታወቀ፡፡
ኤጀንሲው ሰሞኑን ባወጣው ወርኃዊ አገር አቀፍና የክልሎች የሸማቾች መመዘኛ ኢንዴክስ መረጃ መሠረት፣ የጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 34.2 በመቶ፣ የምግብ ዋጋ ግሽበት 40.7 በመቶ፣ እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ግብዓቶች የዋጋ ግሽበት 25.3 በመቶ ነው፡፡
የጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም. የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጋር ሲነፃፀር በ40.7 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት እንዲሁ ካለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጋር ሲነፃፀር በ34.2 ከመቶ ከፍ ብሏል፡፡
በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም. አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 34.8 በመቶ ደርሶ የነበረ መሆኑን፣ በጥቅምት ወር ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 34.2 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ በመስከረም ወር አጠቃላይ የምግብ ዋጋ 42 በመቶ በመድረስ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቶበት እንደነበር፣ ጥቅምት ላይ 1.3 በመቶ ያህል መቀነሱ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆነ ገብዓቶች የዋጋ ግሽበት በመስከረም ወር ከነበረው አኃዝ ብዙም ለውጥ ያላሳየ እንደነበረና 25.2 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ኤጀንሲው ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል፡፡
Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/article/23744