ጁንታው ሚሌን በጦርነት መያዝ እንደማይችል ሲያውቅና ተስፋ ሲቆርጥ በሀሰተኛ ወሬ ሚሌ ተቆጣጥረናል እያለ የውሸት በፕሮፖጋንዳውን መለፍለፍ ጀምሮል
Posted: 15 Nov 2021, 02:47
#Ethiopia : ሰሞኑን ሚሌን ለመያዝ ብሎ አሰፍስፎ የመጣው የጁንታ ሀይል በአፋር በተለያየ አካባቢዎች ላይ ጦርነት ቢያደርግም በጀግኖቹ የአፋር ልዩ ሀይልና የሀገር መከላከያ ባደረጉት ተጋድሎ መቼም ሚሌን መያዝ እንደማይሳካለት አሳይተውታል።
ሆኖም ጁንታው ሚሌን በጦርነት መያዝ እንደማይችል ሲያውቅና ተስፋ ሲቆርጥ በሀሰተኛ ወሬ ሚሌ ተቆጣጥረናል እያለ የውሸት በፕሮፖጋንዳውን መለፍለፍ ጀምሮል እንኳን ሚሌ ሊገባ ይቅርና ቡርቃ መግባት ያቃተው ጁንታው ዛሬም የሞት ሞቱን ከባቲ ተራራዎች ላይ ሁኖ በርቀት በኤሊውሀ እና ካሳጊታ ከተማዎች ላይ የከባድ መሳሪያ በመተኮስ የተስፋ መቁረጥ ሙከራውን እያደረገ ይገኛል፡፡
በአሁን ሰአት ጁንታው የአፋርን መሬቶች እንደማይዝ ስለተረዳ ያለው አማራጭ ወደ ትግራይ ለመመለስ ባገኘው ቦታ በሙሉ የፈሪ ዱላ አይነት ተኩሶችን እየተኮሰ በአፋር ልዩ ሀይል ሚሊሻና መከላክያ እየተደመሰሰ ይገኛል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
