"ወሎየዎች በሶስቱም አቅጣጫ ህይወታቸውን ለማትረፍ በእግር ተጉዘው በሄዱበት ከተማ ሁሉ የብልፅግና ካድሬዎች "ጁንታ" እያሉ እንደሚያሸማቅቋቸው ሲነግረኝ በጣም አዘንኩ።"
Posted: 11 Nov 2021, 09:25
By Abdu Yimer Abegaz
አንድ ወዳጄ ደውሎ ወሎየዎች በሶስቱም አቅጣጫ ህይወታቸውን ለማትረፍ በእግር ተጉዘው በሄዱበት ከተማ ሁሉ የብልፅግና ካድሬዎች "ጁንታ" እያሉ እንደሚያሸማቅቋቸው ሲነግረኝ በጣም አዘንኩ።
አሁን ማን ይሙት ትህነግ ራሱ "ማን ይቀርብኃል? /አንተን ማን ይመስላል?/ ቢሉት በየደረጃው ያለ ስግብግብና ሀገር ሻጭ የብልፅግና ካድሬ እንደሚል ከኛ የሚሰወር መስሏችሁ ነው። ታዲያ የብልፅግና ካድሬዎች አፋችሁን ሞልታችሁ ወሎየን ጁንታ የምትሉት በምን ሞራላችሁ ነው። ገመናችሁን በሸፈነ! ድክመታችሁን በሞላ!
እድሜ ለዶ/ር አብይ ይቅርታ ጠይቆ አፉ ባትባሉ ኖሮ በዚህ ሰዓት መገኛችሁ የት እንደነበር የማናውቅ ከመሰላችሁ ተሳስታችኃል። የወሎየን ኢትዮጵያዊነት እንኳን እናንተ ይቅርና ጁንታው ራሱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቶት አያውቅም፣ አያስገባውምም።
ዝምታችን ለሀገር ነውና ቁስላችንን እየነካካችሁ ህመማችንን አታባብሱት። ለኢትዮጵያ ስንል የከፈልነውን ዋጋ በርካሽ ግብራችሁ ለመለካት አይዳዳችሁ። ይህን ታላቅ ሀገር የመምራት ስልጣን በታሪክ አጋጣሚ በእጃችሁ ገብቷልና በንግግርና በተግባራችሁ አታሳቁን።
እመኑኝ! ይህ ቀን አልፎ ሁሉም አንገቱን ቀና አድርጎ ሲሔድ የዘራችሁትን ታጭዱታላችሁ። አፋችሁ ከመከፈቱ በፊት ካንደም ሁለት ሶስቴ አስቡበት። የምትሰሩት ሁሉ ካለንበት የከፋ ለትውልድ የሚሻገር በሽታ ነውና መንግስት ካድሬዎቹን ይፈትሽ እላለሁ።

Please wait, video is loading...