"ከሚወራውና ከሚናፈሰው አንፃር ደሴና ኮምቦልቻ ደህና ናቸው። በተለይ ግድያን በተመለከተ ከመጀመሪያወቹ ፪ ቀናት ወድህ እንደቆመና ከተሞቹን ራሳቸው አመራር መርጠው እያስተዳደሩ ነው"
Posted: 10 Nov 2021, 19:28
ስለ ደሴና ኮምቦልቻ ለተጨነቃችሁና በውስጥ ደጋግማችሁ ስለምትጠየቁን ወገኖች!!
=============================
ሊንኩን ተጭነው ይገቡ https://t.me/joinchat/XM60pFp-5BE5MDRk
ደሴና ኮምቦልቻ በወራሪው ሀይል ከተያዙ ዛሬ 12 ቀን ሆኗቸዋል።ከተሞቹ ከተያዙ ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የስልክም ሆነ የመብራት አገልግሎት በመቋረጡ ሁሉም ከቤተሰቡ ከዘመድ አዝማዱ ጋር ተለያይቷል።በርግጥ ይህ ከደሴና ኮምቦልቻ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ወሎ ለአራቱም ዞኖች ለ47ቱም ወረዳወች ነው።አጠቃላይ የወሎ ህዝብ ሁሉም ከቤተሰቡ ጋር ተለያይቶ በጭንቀትና ሰቀቀን ላይ መኖር ከጀመረ ሰበባብቷል።ለሰሜን ወሎና ዋግ ደግሞ ከ100 ቀናቶች በላይ ተቆጥሯል።
አስቡት ልጆች እናትና አባቶቻቸውን፣ወላጆች ልጆቻቸውን፣ወንድም እህቱን ይኑር ይሙት ይራበው ይጥማው ሳያውቅ በጭንቀትና በሰቀቀን 4 ወር!!!
ደሴና ኮምቦልቻን በተመለከተ ከተያዙ ማግስት ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያም ሆነ በመንግስት ሚድያወች ብዙ አይነት የአሉሽ አሉሽ ወሬወች ተወርተዋል።እስከ አሁን ድረስም ያለ ምንም መረጃ በመሰለኝና ደሳለኝ ብዙ አይነት ወሬወች በመናፈስ ላይ ናቸው።
ስለ ደሴና ኮምቦልቻ በተደጋጋሚ የተጣራ መረጃ ለማግኘት የሞከርን ሲሆን ብዙወቹ ተጨባጭ ያልሆኑና እንድህ ነው ተብለለው ለማውራት ብቁ ያልሆኑ በመሆናቸው ለሚድያ አላዋልናቸውም።ትላንት ዕለተ ማክሰኞ ግን ከዛው አቆራርጦ የመጣ አንድ ሰው አግኝተን ሁኔታወችን ለማጣራት ሞክረናል።ምንም እንኳ በጠላት እጅ የወደቁ ቢሆንም ከሚወራውና ከሚናፈሰው አንፃር ከተሞቹ ደህና ናቸው። በተለይ ግድያን በተመለከተ ከመጀመሪያወቹ 2 ቀናት ወድህ እንደቆመና ከተሞቹን ራሳቸው አመራር መርጠው እያስተዳደሩ እንደሆነ ገልፆልናል። በከተሞቹ ላይ ያለው ማህበረሰብ በግዳጅ ሱቆችን እንድከፍት ተደርጎ እየተገበያየም እንደሆነ ገልፆልናል መንገደኛው።
በተረፈ ጦርነቱ ጦርነቱ ከከተሞቹ ወጥቶ ከሚሴን አልፎ ካራቆሪ አካባቢና ምዕረብ ወረዳ ቦረና አካባቢ እንደሆነ ያለው አረጋግጠናል።
በአሁኑ ሰዐት አጠቃላይ ወሎ በወራሪው ሀይል ቁጥጥር ሲሆን ደሴና ኮምቦልቻ ከሰሜን ወሎ መጥተው የነበሩት ተፈናቃዮችም በእግራቸው በብዙ ስቃይ እየተንገላቱ እየተመለሱ እንደሆነ አረጋግጠናል።
አጠቃላይ ወሎና በወሎ ህዝብ ላይ የደረሰውን መከራ ማንም ሊረዳው አልቻለም።እንዳውም አንዳንዶች የኢትዮጵያ ጉዳይ ሳይሆን የወሎ ብቻ ጉዳይ አድርገውታል።በተለይም የክልሉ መንግስት ወሎ በእሱ ክልል ውስጥ የሚተዳደር ቀጠና አልመስልህ ካለው ቆይቷል።
የተሻለ መረጃ ይዘን እስከምንመጣ ሰላም እደሩ።ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!!
የወሎ ድምፅ Voice Of Wollo

Please wait, video is loading...