ሰበር ዜና፡ በኢትዮጵያ አንድ የተሌቪጅን Tv ጣቢታ ሁከት እና አመፅ የሚያስነሳ ዘገባ በማስተላለፉ እንዲዘጋ ተደረገ
Posted: 10 Nov 2021, 13:04
የቀድሞ የህፃናትና ሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ የግል ንብረት የነበረው እና በሶማሌ ክልል መዲና ቢሮውን ያደረገው ነበድ ቲቪ ሁከት እና አመፅ የሚያስነሳ ዘገባ በማስተላለፉ መዘጋቱ ተሰምቷል፡፡
ምንጮች ከስፍራው እንዳረጋገጡት ጣቢያው የሀገሪቱን የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ በመጣስ እና አሁን ሀገሪቷ ያለችበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባለማስገባት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅን ተላለፎ በትላንትናው እለት ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ ዘገባ በማሰራጨቱ ነው እንዲዘጋ የተደረገው፡፡
ነበድ የተሰኘው ይሄው ቴሌቭዥን ጣቢያ በትላትና ዘገባው በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም፣ መጤ ባሏቸው የሌላ ብሄር ተወላጆች ምክንያት የክልሉ ህዝብ ጥቅም ተወስዷል፣ ከሌላ ቦታ ፈልሰው የመጡ ሰዎች የክልሉን ወጣቶች የስራ እድል አሳጥተዋል በሚል በክልሉ በሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ሢቀሰቅስ ነበረ የተባለ ሲሆን በክልሉ የሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች በክልሉ መኖር የለባቸውም የሚል በመንግስት እና ህዝብ መካከልም ሁከት እንዲፈጠር በአስቸኳይ አዋጁ የተከለከለ እና ህገወጥ ዘገባ በማስተላለፉ ምክንያ ሊዘጋ እንደቻለ ታውቋል፡፡
የጣቢያው ባለቤት በመንግስት ስልጣን ላይ እያሉም ጣቢያው በክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመካድ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ዘገባዎችን ሲያስተላልፍ ነበር ያሉት ምንጮች በዚህ ያልተገባ ድርጊቱም ከክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደደረሰው እና ከዛም አልፎ ይህን ያልተገባ አሰራር እንዲያስቆም ለ ብሮድካስት ባለስልጣን ባለፈው አመት ደብዳቤ ተፅፎ እንደነበር ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጣቢያው በትላንትናው እለት አንዳንድ የክልሉን ነዋሪዎች አነጋገርኩ ብሎ ባቀረበው ዘገባ ምክንያት የሶማሌ ክልል አስቸኳይ ግዜ አዋጅ ኮማንድ ጣቢያው ባስተላለፈው ብሄር ከብሄር የሚያጋጭ እና ሁከት ቀስቃሽ ዘገባ በህግ እንዲጠየቅ እና ጣቢያው እንዲዘጋ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ይህን ተከትሎ የጣቢያው ባለቤት እና ቀድሞ የሴቶችና ህፃናት ሚስትሯ ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ በቲውተር ገፃቸው እኔ እና ቤተሰቦቼ በኢትዮጵያ የፀጥታ ሓይሎች ምክንያት አደጋ ውስጥ ነን የሚል ፅሁፍ ማጋራታቸው መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
ግለሰቧ ቀደም ሲል 6ተኛው ሃገራዊ ምርጫን ተከትሎ የአዲስ ሚኒስትሮች ሹመት አንድ ሳምንት ሲቀረው ባልተለመደ ሁኔታ የስራ መልቀቂያ በቲውተር ገፃቸው ላይ መለጠፋቸው በበርካቶች ዘንድ ሲያስወቅሳቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
01/03/2014
ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ