Page 1 of 1

ዛሬ ዜናው ሁሉ የድል ነው::መከላከያ አሁንም ያለበትን ችግር ሊፈትሽ ይገባል::የዘመቱ አማራዎች ያለምክንያት ካምፕ መግባት ወይም መቀመጥ የለባቸውም:: የተዘረፈ ንብረት የያዙ መኪናዎች ይመቱ

Posted: 10 Nov 2021, 12:42
by Abaymado
መከላከያ አሁን ያለው አቅዋም ለዚህ አጠራጣሪ ወቅት አድርሶናል:: ብዙ ችግር አለበት:: ወታደሮች እንደሚከዱም ይነገራል:: አመራሮች ራሳቸው አሻጥር ሰርተው አገርን አደጋ ላይ ይጥላሉ::

አሁን ለአገሪቱ ያለው ዋና ዋርካ አማራ ነው :: በፍላጎቱ የሚዘምተው አማራ ነው:: እናም አማራ ላይ ተስፋ ማረግ ይገባ ነበር::

እደግመዋለሁ :
ያለ አማራ እና ያለ አፋር: መከላከያ አስተማማኝ አይደለም:: ድል የሚመጣው በፍላጎት ሲሆን ነው::

ሌላው ጠንካራ ኃይላችን አየር ኃይሉ ነው::አየር ኃይሉ ምንም እንከን አይወጣለትም::

ያለእነዚህ ሶስቱ አገሪቱ አልቆላት ነበር::

አሁንም የምለው መከላከያ ራሱን ይፈትሽ:: መዘናጋት ይብቃ:: የአማራ ልዩ ኃይል ከዘመተ በህዋላ ወደ ስራው ሳይገባ ሞራሉን ማላሸቅ ይብቃ:: የዘመተው አማራ ወያኔን እንዲገጥም ቦታው ይለቀቅለት::


ወያኔ የዘረፈውን ንብረት ወደ ትግራይ ለመውሰድ ቢፈልግም: ቆቦ በፋኖ በመያዝዋ መሄጃ እንዳጣ ይነገራል: እናም መኪኖቹ ተሰልፈው እንደቆሙ ነው የሚነገረው:: እናም የሆነ ኃይል ደርሶ የሆነ ነገር ማረግ አለበት::

Re: ዛሬ ዜናው ሁሉ የድል ነው::መከላከያ አሁንም ያለበትን ችግር ሊፈትሽ ይገባል::የዘመቱ አማራዎች ያለምክንያት ካምፕ መግባት ወይም መቀመጥ የለባቸውም:: የተዘረፈ ንብረት የያዙ መኪናዎች

Posted: 11 Nov 2021, 08:33
by Abaymado
ያልነው ትክክል ነው::
ቆቦዎች ወያኔ የዘረፈውን ንብረት እንዳያሳልፍ አርጎታል::

ወያኔ የሞቱትን መቀሌመቅበር አቁሟል::