****************
በትላንትናው እለት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የጉምዝ ታጣቂዎች የወረዳው ዋና መቀመጫ በሆነችው ድባጤ ከተማ አቅራቢያ በከፈቱት ተኩስ ከአራት ሰዎች በላይ መገደላቸውን የአይን እማኞች ለየኛ ቴሌቪዥን ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት, ትላንት ሰኞ ማለትም ጥቅምት 29 ማለዳ ጀምሮ በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫ በታጣቂዎች የተከፈተው የተኩስ እሩምታ እስከ አመሻሹ ድረስ እንደነበርም ነው የገለፁት።
ታጣቂዎቹ ወደ ከተማዋ ለመግባት በአራቱም አቅጣጫ ሙከራ ሲያደርጉ እንደ ላውንቸርና ሌሎች ከባባድ መሳሪያዎችን ሲተኩሱ እንደነበረ የገለፁልን እማኞቻችን, በዚህም የአከባቢው ነዋሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጨንቆ እንደነበርም ተናግረዋል።
ከትላንት ማታ ጀምሮ የመንግስት ፀጥታ ሃይሎች በታጣቂዎቹ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተከትሎ ታጣቂዎቹ ወደ ከተማዋ መተኮሳቸው አቁመው መበተናቸውንም የተናገሩት ነዋሪዎቹ, ነገር ግን እነዚህ ታጣቂዎች እስከመጨረሻው እስካልተደመሰሱ ድረስ ሁሌም ስጋት ላይ ነን ብለዋል።
30/02/2014
ጠቃሚ የጤና ትምህርት
የልብ ድካም መንስኤዎችና መከላከያ ወሳኝ መንገዶች። ለጥንቃቄ መታየት ያለበት። መፍትሄዉ በእጃችን ነዉ:: ለማየት ሊንኩን ወይም ምስሉን ይጫኑ