Page 1 of 1

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ሁለት የጠላት ታርጌቶች በአየር ሃይል ተመቱ!

Posted: 08 Nov 2021, 12:12
by Ejersa
በራያና ሃጂ ሜዳ (ኪሊዋ) የሚገኙ የህወሓት የሽብር ቡድን ማሰልጠኛዎች በአየር ኃይል መመታታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ እንደተመላከተው÷ በራያ አካባቢ አረዳ ባታ የሚገኘው የህወሓት ሽብር ቡድን ማሠልጠኛ የሆነው በአየር ሃይል ተመትቷል።

በማሠልጠኛው በአሁኑ ወቅት ለሽብር ተልእኮ የተመለመሉ በርካታ ታጣቂዎች እያሠለጠኑበት እንደነበርም ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በሰሜን ወሎና አፋር አዋሳኝ ኪሊዋ ወይም ሃጂሜዳ የሚገኘው የሽብር ቡድኑ የስልጠና እና የሎጅስቲክስ ማከማቻ እንዲሁም የጠላት ተጠባባቂ ሃይል በአየር መመታቱን መግለጫው አመላክቷል፡፡